87 የካናዳ ሴናተሮች ላይ ማዕቀብ መጣሉን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአሜሪካ የምክር ቤት አባላት እና በካናዳ ሴናቶሮች ላይ ማዕቀብ መጣሉን በትናትናው እለት አስታውቋል።
እንደ ሚኒስቴሩ መግለጫ፤ ማዕቀቡ በ398 የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት እና በ87 የካናዳ ሴናተሮች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል።
ሩሲያ ውሳኔውን ያሳለፈችው የአሜሪካ አስተዳደር በ328 የሩስያ ተወካዮች ምክር ቤት (ዱማ) አባላት ለጣለው ማዕቀብ አጸፋ መሆኑ ተነግሯል።
ካናዳም በሁሉም የሩሲያ ፌዴሬሽን አባላት ላይ የጣለችውንመ ማዕቀብ ተከትሎ በሴናተሮቿ ላይ የአፀፋ እርምጅ መወሰዱን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
አሜሪካ ያለማቋረጥ እየጣለች ያለውን ማዕቀብ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሩሲያ ተጨማሪ የአጸፋ እርምጃዎችን ለመውሰድ ዝግጅት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አመላክቷል።
የዋይት ሃውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጄን ፕሳኪ በተመሳሳይ እለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ልዩ ልዩ ማዕቀቦች ለመጣል መዘጋጀቷን አስታውቀዋል።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚረፑቲን በሳለፍነው ማከሰኞ በሰጡት አስተያየት፤ ሩሲያ ለማግለል የሚደረገው ሙከራ አይሳካም ሲሉ ምእራባውያንን ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።
ሩሲያ ባለፈው የፈረንጆቹ የካቲት ወር በዩክሬን የጀመረችውን “ልዩ ወታራዊ ዘመቻ” ተከትሎ ማእቀብ ባዘነቡባት ምእራባውያን እና አሜሪካ ላይ እምነት እንደማይኖራትና ገልጻለች።
ፑቱን በዩክሬን “ወታደራዊ ዘመቻ” ለማድረግ የተገደዱት፤ አሜሪካ ዩክሬንን እና ኔቶን በመጠቀም ለማስፈራራት ስለሞከረች እና ይህንም መከላከል ሲለሚገባ ነው ብለዋል።