አሜሪካ የሀውቲ አማጺያንን በሽብርተኝነት ለመፈረጅ እያጤነች መሆኗን አስታወቀች
ቀይ ባህር በአለም ላይ እጅግ ስራ ከሚበዛባቸው የንግድ መስመሮች አንዱ ነው ነው
በኢራን የሚደገፉት እና በሰሜን የመን ሰንአን ጨምሮ በርካታ ቦታዎችን የተቆጣጠሩት ሀውቲዎች ባለፉት ሳምንታት በእስራኤል ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል
አሜሪካ የሀውቲ አማጺያንን በሽብርተኝነት ለመፈረጅ እያጤነች መሆኗን አስታወቀች።
የሀውቲ አማጺያን በቀይ ባህር የእቃ ጫኝ መርከብ ይዘናል ማለታቸውን ተከትሎ የአሜሪካ መንግስት ቡድኑን በድጋሚ በሽብርተኝነት ለመፈረጅ እያጤነ እንደሚገኝ አስታውቋል።
የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ምክርቤት ቃል አቀባይ ጆን ክርቢ ባለፈው ማክሰኞ እለት የመርከቧን መታገት አውግዘዋል፤ በአለምአቀፍ ውሃ ላይ ተፈጽሟል ላሉት ወንጀል የሀውቲ አማጺያንን ከሰዋል።
ቀይ ባህር በአለም ላይ እጅግ ስራ ከሚበዛባቸው የንግድ መስመሮች አንዱ ነው ነው።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በሽርብርኝነት የተፈረጁትን የሀውቲ አማጺያን በ2021 ከሽብርተኝነት ዝርዝር ውስጥ መሰረዛቸው ይታወሳል።
ተመድ እና የእርዳታ ድርጅቶች የሽብርተኝነት ፍረጃው በጦርነት ለተጎዳችው የመን የሚደረገውን የእርዳታ አቅርቦት ያውካል የሚል ትችች ሲያቀርቡ ቆይተዋል።
በኢራን የሚደገፉት እና በሰሜን የመን ሰንአን ጨምሮ በርካታ ቦታዎችን የተቆጣጠሩት ሀውቲዎች ባለፉት ሳምንታት በእስራኤል ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል።
ከእስራኤል ጋር እየተዋጋ ላለው ሀማስ ድጋፋቸውን የገለጹት ሀውቲዎች በእስራኤል ላይ የድሮን እና ሚሳይል ጥቃት ማድረሳቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።
አማጺያኑ በቀይ ባህር በሚደረግ የመርከብ እንቅስቃሴ ላይ ጥቃት እንደሚሰነዝሩ እያስፈራሩ ናቸው።
አማጺያኑ ከቀናት በፊት ከእስራኤል ባለሀብት ጋር ግንኙነት አላት ያሏትን ጋላክሲ ሌደር የተባለችውን መርከብ ይዘዋል።
በመርከቧ ላይ የነበሩት የተለዩየ ሀገራት ዜግነት ያላቸው ሰራተኞችም እስካሁን በሀውቲዎች እጅ ይገኛሉ።
የባይደን አስተዳደር የሽበርተኝነት ፍረጃውን ያነሳው ቡድኑ ከመንግስት እና ከ2015 ጀምሮ ሳኡዲ ከምትመራው ጥምረት ጋር ግጭት ውስጥ ስለቆየ እርዳታ ማስገባት አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት ነበር።