በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት የሁቲ አማጺያን ከሐማስ ጎን በመሆን እስራኤልን በማጥቃት ለይ ናቸው
አሜሪካ እና ብሪታንያ በየመን የሁቲ ይዞታዎችን ደበደቡ፡፡
አንድ ዓመት ሊሆነው ሶስተ ቀናት ብቻ የቀሩት የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት አሁንም የቀጠለ ሲሆን ኢራን እና እስራኤል ወደ መደበኛ ጦርነት እንዳይገቡ ተሰግቷል፡፡
ባለፉት ሶስት ሳምንታት በሊባኖሱ ሂዝቦላህ ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት የከፈተችው እስራኤል በትናንትናው ዕለት በኢራን ሚሳኤል ተመታለች፡፡
በኢራን እንደሚደገፉ የሚታመነው የየመኑ ሁቲ አማጺያን ከሰሞኑ በእስራኤል ላይ የሮኬት ጥቃት ማድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡
የእስራኤል ዋነኛ አጋር የሆኑት አሜሪካ እና ብሪታንያ በሁቲ ዋነኛ ይዞታዎች ናቸው በተባሉ ስፍራዎች ላይ የአየር ላይ ድብደባ ፈጽመዋል፡፡
የየመን ሁቲ አማጺያን የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን መተው ጣሉ
በዛሬው ዕለትም በየመን መዲና ሰነዓ ከተማ እና በሆዴዳህ ወደብ ላይ የአየር ላይ ድብደባ እንደፈጸሙ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ የአየር ድብደባው ከሰነዓ እና ሆዴዳህ ወደብ በተጨማሪም በዳማር ከተማ ላይ ተፈጽሟል ተብሏል፡፡
ይሁንና ብሪታንያ ዛሬ በየመን በተካሄደው የአየር ላይ ጥቃት እንዳልተሳተፈች አሳውቃለች፡፡
በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት እየጨመረ ሲሆን መስከርም ወር ላይ ዋጋው ቀንሶ የነበረው ዓለም ነዳጅ ዋጋ ዳግም በማሻቀብ ላይ ይገኛል፡፡
የሐማስ-እስራኤል ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የቀይ ባህር ባህር ትራንስፖርት መስተጓጎል የገጠመው ሲሆን ግብጽ ከስዊዝ ካናል ታገኘው የነበረው ገቢ በ60 በመቶ እንደቀነሰባት አስታውቃለች፡፡