የብድር ጣሪያውን ከፍ ለማድረግ ሪፐብሊካኖች እና ዴሞክራቶች የገቡበት ፍጥጫ እስካሁን መፍትሄ አላገኘም
የአሜሪካ የፌደራል መንግስት እዳ በየካቲት ወር 2022 30 ትሪሊየን በመድረስ በታሪክ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።
በ2023 ደግሞ 31 ነጥብ 4 ትሪሊየን መድረሱን መረጃዎች ያሳያሉ።
ልዕለ ሃያሏ ሀገር በሁለቱ የአለም ጦርነቶች እና በተለያዩ ሀገራት ጦርነቶች በነበራት ተሳትፎ ምክንያት ያጋጠማትን የበጀት ጉድለት ለመሸፈን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ተበድራለች።
የአፍጋኒስታን እና ኢራቅ ጦርነት፣ የ2008ቱ የኢኮኖሚ ቀውስ እና የኮሮና ወረርሽኝ የሀገሪቱን ብሄራዊ እዳ ከፍ እንዲል እንዳደረጉትም ይነገራል።
በሁለት አስርት አመታት ውስጥ 25 ትሪሊየን ዶላር እዳ ያስመዘገበችው አሜሪካ እዳዋ በቀጣዮቹ አስር አመታት በየአመቱ በ1 ነጥብ 3 ትሪሊየን ዶላር እንደሚጨምር የሀገሪቱ ግምጃ ቤት አስታውቋል።
የብድር ጣሪያውን ከፍ ለማድረግ ሪፐብሊካኖች እና ዴሞክራቶች የገቡበት ፍጥጫም እስካሁን መፍትሄ አላገኘም።
ያለፉትን 90 አመታት የአሜሪካ የመንግስት እዳ እድገትን ይመልከቱ፦