የሀገሪቱ ህግ መወሰኛው ምክር ቤት የአሜሪካ ብሔራዊ እዳ ጣሪያ ሊወስን ይገባል ተብሏል
የአሜሪካ ብሔራዊ እዳ መጠን ከ31 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ደረሰ።
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር አሜሪካ የእዳ መጠኗ ከ31 ትሪሊዮን ማለፉን የሀገሪቱ ግምጃ ቤት በድረገጹ አስታውቋል።
የሀገሪቱ የእዳ መጠን በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛው እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን የዋጋ ግሽበት መፈጠሩ የመንግስት የሚበደረውን የገንዘብ መጠን እንዲጨምር አድርጓል ተብሏል።
የአሜሪካ መንግስት እዳ መጠን ባሳለፍነው ጥር ላይ 30 ትሪሊዮን ደርሶ የነበረ ሲሆን ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ተጨማሪ 1 ነጥብ 1 ትሪሊዮን ዶላር ተጨማሪ ብድር መበደሩ ተገልጿል።
የአሜሪካ ብሔራዊ እዳ መጠን መጨመሩን ተከትሎም የሀገሪቱ ህግ መወሰኛው ምክር ቤት በመንግስት ላይ ተጨማሪ ብድር እንዳይበደር ጣሪያ ሊጥል እንደሚገባም ተገልጿል።
ባሳለፍነው ዓመት መንግስት 2 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ዶላር እንዲበደር መንግስት ከዚህ ምክር ቤት ፈቃድ አግኝቶ ነበር።
መንግስት ለተለያዩ ጉዳዮች ማስፈጸሚያ ከባንኮች የሚበደረው ብድር ከ31 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር እንዳያልፍ በኮንግረሱ እገዳ ሊጣልበት እንደሚችል የሀገሪቱ ፖለቲከኞች በመናገር ላይ ናቸው።
የአሜሪካ ብሔራዊ እዳ መጠን ከ31 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ደረሰ።
የዓለም ልዕለ ሀያል ሀገር አሜሪካ የእዳ መጠኗ ከ31 ትሪሊዮን ማለፉን የሀገሪቱ ግምጃ ቤት በድረገጹ አስታውቋል።