የአሜሪካ ዕለታዊ ብድር 5 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ተብሏል
የአሜሪካ ብሔራዊ እዳ መጠን 35 ትሪሊዮን ዶላር አለፈ፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር አሜሪካ የእዳ መጠኗ ከ35 ትሪሊዮን ማለፉን የሀገሪቱ ግምጃ ቤት በድረገጹ አስታውቋል።
የሀገሪቱ የእዳ መጠን በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛው እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን የዋጋ ግሽበት መፈጠሩ፣ ለዩክሬን እና እስራኤል የተሰጠው እርዳታ በየጊዜው መጨመር እና የፊታችን ሕዳር ወር ለይ የሚደረገው ምርጫ መንግስት የሚበደረውን የገንዘብ መጠን እንዲጨምር አድርጓል ተብሏል።
የአሜሪካ መንግስት እዳ መጠን ባሳለፍነው ጥር ላይ 34 ትሪሊዮን ደርሶ የነበረ ሲሆን ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ አንድ ትሪሊዮን ዶላር ተጨማሪ ብድር መበደሩ ተገልጿል።
አሜሪካ ያለባት ብድር ከጠቅላላ ዓመታዊ ምርቷ በላይ ነው የተባለ ሲሆን ብድሩ ከዓመታዊ እድገቱ ጋር ሲነጻጸር 120 በመቶ ደርሷል ተብሏል፡፡
አዲሱ የአሜሪካ እጩ ምክትል ፕሬዝዳንት ልጅ የማይወልዱ ሴቶችን የወረፉበት ንግግር ቁጣን ቀስቅሷል
የሀገሪቱ ብድር መጠን በዚሁ ከቀጠለ በ2054 የአሜሪካ ጠቅላላ ብድር ከዓመታዊ እድገቱ ጋር ሲነጻጸር 166 በመቶ ያህል እንደሚጨምር ተገልጿል፡፡
የብድር መጠን መጨመሩን ተከትሎ በርካታ አሜሪካዊያን ፖለቲከኞች እና ነጋዴዎች ተቃውሟቸውን የገለጹ ሲሆን ጉዳዩ መፍትሔ እንደሚያሻው በመናገር ላይ ናቸው፡፡
አሁን ለይ የአሜሪካ መንግስት በየቀኑ አምስት ቢሊዮን ዶላር እየተበደረ ነው የተባለ ሲሆን ቢሊየነሩ ኢለን መስክ ይህ እብደት ነው ሲል በኤክስ አካውንቱ ላይ ጽፏል፡፡