አሜሪካ በሚሲሲፒ ግዛት የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች
በግዛቱ ላይ ሀይለኛ አውሎ ንፋስ በመውደቁ በትንሹ 25 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል

በአሜሪካ በተለያየ ጊዜ በሚከሰተው አውሎ ንፋስ አደጋዎች አስተናግዳለች
ኘሬዝደንት ባይደን በአውሎ ንፋስ አደጋ ምክንያት ለሚሲሲፒ ድንገተኛ አደጋ አወጀ
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እሁድ እለት በሚሲሲፒ ላይ በጣለው ከባድ አውሎ ንፋስ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አጽድቀዋል።
በግዛቱ ላይ ሀይለኛ አውሎ ንፋስ በመውደቁ በሚሲሲፒ በትንሹ 25 ሰዎች እና አንድ በአላባማ ከሞቱ በኋላ ነው አሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀው።
ዋይት ሀውስ እንዳስታወቀው ባይደን የፌደራል ዕርዳታ የአካባቢ መልሶ ማቋቋሚያ ጥረቶችን እንዲጨምር አዝዘዋል።ገንዘቡ በካሮል፣ ሃምፍሬይስ፣ ሞንሮ እና ሻርኪ አውራጃዎች ውስጥ ለተጎዱ ሰዎች ይሰጣል ሲል መግለጫው ገልጿል።
በአሜሪካ በተለያየ ጊዜ በሚከሰተው አውሎ ንፋስ አደጋዎች አስተናግዳለች።