በአሜሪካ አርካንሳስ እና ኬንታኪ ግዛቶች በደረሱ ከባድ የአውሎ ንፋስ አደጋዎች 100 ሰዎች ሳይሞቱ አልቀረም ተባለ
ከባድ አውሎ ንፋሱ በርካታ የንግድ እና መኖሪያ ቤቶችን ያወደመ ሲሆን ተጨማሪ ሞቾች ሊኖሩ ይችላሉ ተብሏል

በዚህ ወቅት ተከስቶ አያውቅም የተባለለት ይህ አደጋ በአሜሪካ ታሪክ ብዙ ሰዎች የሞቱበት ነው ተብሏል
በአሜሪካ አርካንሳስ እና ኬንታኪ ግዛቶች በደረሱ ከባድ አውሎ ንፋስ አደጋዎች 100 ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተገለጸ፡፡
በግዛቶቹ በደረሱት ከ20 በላይ ከባድ አውሎ ንፋሶች እስከ መቶ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡
አሜሪካ ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ ለ12 ጊዜ ዜጎቿ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ አስጠንቅቃለች
ይህ አደጋ በዚህ ቀዝቃዛ የአየር ንብረት በሚታይበት ወቅት የተከሰተ ከባድ የአውሎ ንፋስ አደጋ መሆኑም ተገልጿል፡፡
አሜሪካዊው ቢሊየነር ቢል ጌትስ የኮሮና ቫይረስ የሚጠፋበትን ጊዜ ተነበዩ
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ሌሊቱን ሳይቀር የተጎጂዎችን ህይወት ለማትረፍ እየጣሩ ናቸው የተባለ ሲሆን በአደጋው ሳቢያ ህይወታቸውን ያጡ ተጨማሪ ዜጎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ዘገባው አክሏል፡፡
በኢሊኖይስ ዩኒቨርሲቲ የአየር ንብረት ተመራማሪው ቪክተር ገንሲሰኒ እንዳሉት በታህሳስ ወር አየሩ የሚቀዘቅዝበት እና የአውሎ ንፋሱን ፍጥነት ይቀንሰው ነበር እንደዚህ አይነት የአውሎ ነፋስ አደጋ ያልተለመደ ነው፡፡
አሜሪካን ጨምሮ ስድስት ሀገራት “ኢትዮጵያ ማንነት ላይ ያተኮረ የሚመስል እስር እንድታቆም”አሳሰቡ
የአሁኑ ከባድ የአውሎ ንፋስ አደጋ በአርካንሳስ እና ኬንተኪ ግዛቶች የከፋ ጉዳት ያድርስ እንጂ በአጠቃላይ በአምስት ግዛቶች ነው ያጋጠመው፡፡
የኬንታኪ ግዛት አስተዳዳሪ አንዲ በሽር በበኩላቸው በዚህ አስከፊ አውሎ ንፋስ አደጋ ምክንያት ከ70 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን ተናግረው የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊያልፍ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
በአሜሪካ ታሪክ በፈረንጆቹ 1925 ዓመት በሰዓት 365 ኪሎ ሜትር ፍጥነት ያለው ከባድ አውሎ ንፋስ በሚዙሪ፣ ኢሊኖይስ እና ኢንዲያና ግዛቶች ተከስቶ 695 ሰዎች ሲሞቱ ከ15 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶች ደግሞ ወድመዋል፡፡