አሜሪካ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች የጦር ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ድምዳሜ ላይ ደረሰች
ብሊንከን አረብ ያልሆኑ የማሳሊት ጎሳ ንጹሃን ታድነው እየተገደሉ ነው ብለዋል
ውሳኔው የተደረሰው፣ ጦርነቱ እንዲያቆም እየተደረገ የነበረው ድርድር በድጋሚ ከመቋረጡ በኋላ ነው
አሜሪካ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች የጦር ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ድምዳሜ ላይ ደረሰች።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በትናንትናው እለት እንደተናገሩት አሜሪካ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች የጦር ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሷን ተናግረዋል።
ብሊንከን እንደናገሩት ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች እና አጋር የሆኑ ታጣቂዎች በሰብአዊነት ላይ ወንጀል እና የዘር ማጽዳት ፈጽመዋል።
በሚያዝያ ወር የጀመረው ጦርነት 6.5 ሚሊዮን ሰዎች በሱዳን ውስጥ እና ከሱዳን ውጭ እንዲፈናቀሉ፣ 10ሺ ሰዎች እንዲገደሉ እና ኢኮኖሚው እንዲደቅ አድርጓል።
"ሁለቱ ተፋላሚዎች ውጊያውን አሁኑኑ እንዲያቆሙ፣ በአለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ህግ እንዲገዙ እንዲሁም ግፍ የፈጸሙት ተጠያቂ" እንዲደረጉ ብሊንከን ጥሪ አቅርበዋል።
የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በዳርፉር የዘር ጭፍጨፋ በማድረግ እና በካርቱም ደግሞ ዝርፊያ እና አስገድዶ መድፈር በመፈጸም ይከሰሳሉ።
ብሊንከን አረብ ያልሆኑ የማሳሊት ጎሳ ንጹሃን ታድነው እየተገደሉ ነው ብለዋል።
የሱዳን ጦር፣ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ባሉባቸው ቦታዎች ከባድ የአየር እና የከባድ መሳሪያ ድብደባ በማድረግ አለምአቀፍ ህግን ጥሷል ተብሏል።
ብሊንከን "በጦሩ እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይል እስርቤት ያሉ ታሳሪዎች የመብት ጥሰት ተደርጎባቸዋል፤ የተወሰኑት ተገድለዋል" ብለዋል።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዝርዝር የህግ ሂደት እና ትንተና ካደረገ በኋላ ተፋላሚ ኃይሎቹ የጦር ወንጀል ፈጽመዋል የሚባለው ይፋዊ ድምዳሜ ላይ ደርሷል።
ነገርግን ውሳኔው የሚወሰዱ እርምዳዎችን ያላከተተ በመሆኑ በተፋላሚ ኃይሎች ላይ ወዲያውኑ የሚደርስ ተጽዕኖ የለም።
ውሳኔው የተደረሰው፣ ጦርነቱ እንዲያቆም በአሜሪካ እና በሳኡዲ አረቢያ እየተደረገ የነበረው ድርድር በድጋሚ በመቋረጡ እና ተፋላሚ ኃይሎቹ ውጊውን አጠናክረው ከቀጠሉ በኋላ ነው።