ጦርነቱ እልባት እንዲያገኝ ጥረት የሚያደርጉት የአሜሪካ ዲኘሎማት ለኢትዮጵያውያን የእርቅ አመት ተመኙ
ሙሳ ፋኪ መሃመት አዲሱ ዓመት “የሰላምና የእርቅ” እንዲሆን እንመኛለን ብለዋል
በኢትዮጵያ ለወራት ጋብ ብሎ የነበረው ጦርነት በድጋሚ ተቀስቅሷል
በኢትዮጵያ የተጀረመው ጦርነት በሰላም እንዲፈታ ጥረት እያደረጉ ያሉት የአሜሪካ ዲፕሎማት ማይክ ሀመር በአዲሱ አመት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ተመኝተዋል።
ማይክ ሐመር አዲሱ ዓመት በግጭቱ ውስጥ ያሉ ወገኖች ከጦርነት ይልቅ ንግግሮችን ለመምረጥ ድፍረት የሚያገኙበትና ዘላቂ ሰላም በሚያስገኘ አፍሪካ ህብረት- መር የሰላም ሂደት ላይ የሚሳተፉበት እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡
ማይክ ሀመር በኢትዮጵያ በፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል ያለው ግጭት እንዲፈታ በተደገጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ተመላልሰዋል።
በተመሳሳይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሳ ፋኪ ማህመትም በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት የመልከምአዲስ ምኞት ለኢትዮጵያውያ እርቅ ተመኝተዋል።
ሊቀ መንበሩ "አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን፣የሰላም፣የፈውስ፣የእርቅና የእድገት ዓመት እንዲሆንላቸው ምኞታችን ነው” ብለዋል፡፡
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ እና የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር በትናንትናው እለት ተገናኝተው በኢትዮጵያ የሰላም ሂደት ዙሪያ መምከራቸው የሚታወቅ ነው፡፡
ሙሳ ፋኪ እና ማይክ ሐመር በወይይታቸው የአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያግዝ ለማድረግ ከስምምነት መድረሳቸው አስታውቀዋል።
በኢትዮጵያ በፌደራል መንግስትና እና በህወሓት መካከል ለወራት ጋብ የነበረው ጦርነት በድጋሚ ተቀስቅሷል።