ቃል አቀባዩ ጥቃቱን ያደረሱት በኢራን የሚደገፉት የኢራቅ ታጣቂዎች ናቸው ተብሎ እንደሚታመን ተናግረዋል
በኢራቅ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ በሮኬት ተመታ።
በኢራቅ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ በዛሬው እለት ሁለት ጊዜ በሮኬት መመታቱን የኢምባሲው ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ በጥቃቱ የደረሰ ጉዳት የለም ብለዋል።
ቃል አቀባዩ ጥቃቱን ያደረሱት በኢራን የሚደገፉት የኢራቅ ታጣቂዎች ናቸው ተብሎ እንደሚታመን ተናግረዋል።
እስካሁን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ ቡድን የለም።
የኢራን አጋር የሆኑት የሺያ ሙስሊም ታጣቂዎች ባለፈው ጥቅምት በኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ከደረሱ ወዲህ በኢምባሲው ላይ የተቃጣ የመጀመሪያ የሮኬት ጥቃት ነው።
እስላማዊ እንቅስቃሴ በሚል ስም የሚንቀሳቀሱት ታጣቂ ቡድኖች ያደረሷቸውን 70 ጥቃቶች፣ አሜሪካ እስራኤል በጋዛ ለምታደርገው ጦርነት ካሳየችው ድጋፍ ጋር አያይዘውታል።
የኢምባሲው ቃል አቀባይ በተለያየ አጋጣሚ አንዳደረግነው የኢራቅ መንግስት የዲፕሎማቲክ ተቋማትን ያለውን ኃይል ተጠቅሞ እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።
አሜሪካ ከዲፕሎማቲክ ሰራተኞች በተጨማሪ አይኤስን ለሚዋጉት የኢራቅ ወታደሮች ስልጠናና ምክር ይሰጣሉ ያለቻቸው 2500 ወታደሮች በኢራቅ አስፍራለች።
ቃል አቀባዩ በየትኛውም የአለም ክፍል ያሉ ሰራተኞቻችን ከሚደርስባቸው ጥቃት የመከላከል መብት አለን ሲሉም ተናግረዋል።