
አሜሪካ ማእቀቡን ያነሳችው በቡሩንዲ ያለውን ለውጥ በማየት ነው ተብሏል
በቡሩንዲ በፖለቲከኞች ላይ ከተወሰደው ደም አፍሳሽ እርምጃ በኋላ ያሉ ሁኔታዎች መቀየራቸውን የገለጸችው አሜሪካ በቡሩንዲ ላይ ጥላው የነበረችው የማእቀብ ፕሮግራም ማንሳቷን አስታውቃለች፡፡
ማእቀቡና በ11 ሰዎች ላይ ተጥሎ ነበረው የቪዛ እገዳ መነሳቱንና ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
አሜሪካ ማእቀቡን ያነሳችው፣ፕሬዘዳንት ኢቫርስቴ ኒዲያሽሜይ በኢኮኖሚው ዘርፍ ጭምር ለለውጥ ያላቸውን ተነሳሽነት ከግምት በማስገባት መሆኑን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ገልጸዋል፡፡
ንዳይሽሜ በትዊተራቸው እንደጻፉት የአሜሪካን ውሳኔ በበጎ ተቀብለዋል፡፡
የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ቡሩንዲ የሰብአዊ መብትን ለማስከበር የምታደርገውን ጥረት ማድነቁ በጣም አስፈላጊ ሲሉ የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሆኑት ሲክቴ ቪጅኒ ኒሙራባ ተናግረዋል፡፡
በቅርቡ፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን፤ ኮሚሽኑ በሀገሪቱ የሚያደርገውን ምርመራ አግዷል፡፡ ነገርግን ጥቂት የሰብአዊ መብት ቡድኖች፣ በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ እየተባባሰ ነው ብለዋል፡፡