የአሜሪካ ልዩ መልእክተኛ ፌልትማን ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው፣ከባለሥልጣናት ጋር ይገናኛሉ ተባለ
ፌልትማን በኢትዮጵያ ጉዳይ ከኬንያ ጋር በተደጋጋሚ መወያየታቸው ይታወሳል
አሜሪካ በኢትዮጵያ ተፈጽሟል በተባለው የሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ከአጎአ የንግድ ትስስትር መሰረዟ ይታወሳል
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ፌልትማን ነገ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ፤ከባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ ተብሏል፡፡
የአሜሪካ የአፍካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን በነገው እለት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡና ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ተገልጿል፡፡
ፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት በኢትዮጵያ ያለው ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ለመነጋገር መሆኑን ሮይተርስ አንድ ከፍተኛ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
በአፍሪካ ከፍተኛ ደም አፋሳሽ ግጭቶች መካከል በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት ኃይሎች መካከል የተካሄደው ግጭት ሲሆን አንድ አመት ባስቆጠረው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎችን ተገድለዋል፤በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡
አሜሪካ ግጭቱ እንዲቆም በድርድር እንዲፈታ፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ እንዲቆም እና የሰብአዊ አገልግሎት አቅርቦት እንዲቆም ደጋግማ ጠይቃለች።
ፌልትማን በኢትዮጵያ ጉዳይ ኬንያን ጨምሮ ከለሎች ሀገራት ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡
አሜሪካ ግጭቱን በመተመለከተ የያዘችው አቋም በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ተቀባይት አላገኘም፡፡ አሜሪካ በኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጽሟል በተባለው የሰብአዊ መብት ጥስት ምክንያት ኢትዮጵያን ከቀረጽና ኮታ ነጻ የንግድ ችሮታ(አጎአ) የንግድ ትስስር መዘረዟ ይታወቃል፡፡
የአሜሪካ መንግስትን ወሳኔ የተቃወመችው ኢትዮጵያ፤ውሳኔው እንዲቀለበስ መጠየቋ ይታወሳል፡፡ ነገረግን እስካሁን በአሜሪካ በኩል የአቋም ለውጥ አልተሰማም፡፡
የኢትዮጵያ መንግሰት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካውጀና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ግንባር ከዘመቱ በኋላ በህወሃት ተይዘው የነበሩ በርካታ የአማራ እና የአፋር ክልል ቦታዎች ነጻ ወጥተዋል፡፡ መንግስት የህወሓት ሀይሎችን በማሸነፍ ይዘዋቸው ከነበሩ ቦታዎች እንዲወጡ ማድረጉን ሲገልጽ ህወሓት በአንጻሩ “ለሰላም እድል ለመስጠት” ሲባል ከአማራ እና አፋር ክልሎች ተዋጊዎቹን ማስወጣቱን ይገልጻል፡፡
ከአንድ አመት በላይ ያስቆጠረው ጦርነቱ በሺዎች ሲገደሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለው ህይወታቸው ተመሰቃቅሏል፡፡