የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ተከሰከሰ
ኤፍ-16 የተሰኘው የአሜሪካ አውሮፕላን በደቡብ ኮሪያ መከስከሱ ተገልጿል
የተከሰከሰው የጦር አውሮፕላን በኮሪያ ልሳነ ምድር መደበኛ ቅኝት በማድረግ ላይ ነበር ተብሏል
የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ተከሰከሰ።
የአሜሪካ መከላከያ ባወጣው መግለጫ ኤፍ 16 የተሰኘው የውጊያ አውሮፕላን በደቡብ ኮሪያ ኦሳን አውሮፕላን ማዘዣ አቅራቢያ ተከስክሷል።
የአውሮፕላኑ አብራሪን ከከፋ ጉዳት መታደግ የተቻለ ሲሆን በአደጋው ሌሎች ንጹሀን ሰዎች ላይ ያደረሰው ጉዳት እንደሌለ ሲኤን ኤን ዘግቧል።
አውሮፕላኑ ከሰሜን ኮሪያ ሊሰነዘር የሚችልን ጥቃት በኮሪያ ባህረ ሰላጤ ቅኝት በማድረግ ላይ እያለ እንደተከሰከሰ ተገልጿል።
ፔንታጎን ለአውሮፕላኑ መከስከስ ምክንያት የሆኑ ነገሮችን በመመርመር ላይ መሆኑን አስታውቋል።
በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን የወጣ የምርመራ ሪፖርት ያልተገኘ ሲሆን ተጨማሪ ምርመራ እንደሚደረግም የሀገሪቱ መከላከያ ገልጿል።
የደቡብ ኮሪያ መንግሥት በበኩሉ የጦር አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት ስፍራ የተከሰተውን እሳት አደጋ ለመቆጣጠር የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎችን ማሰማራቱን አስታውቋል።
ይህ በዚህ እንዳለ አሜሪካ የተከሰከሰው የውጊያ አውሮፕላን አብራሪ ህክምና እየተከታተለ ከመሆኑ ውጪ ማንነቱን እስካሁን ይፋ አላደረገችም