የአሜሪካ መንግስት ለመረጃ ሰጪዎች ዳጎስ ያለ ማበረታቻ መዘጋጀቱን ገልጿል
አሜሪካ ለአንድ መረጃ አሾላኪ 279 ሚሊዮን ዶላር ከፈለች።
የአሜሪካ የደህንነት እና ልውውጥ ኮሚሽን በታሪኩ ትልቅ የሆነውን 279 ሚሊዮን ዶላር ለመረጃ አቀባይ መክፈሉን አስታውቋል።
ኮሚሽኑ ያገኘው መረጃው ህግን ለማስፈጸም እንደረዳው ገልጿል።
ሆኖም ተቆጣጣሪው ክፍያውን ለየትኛው መዝገቡ እንደከፈለ ያለው ነገር የለም።
ክፍያው በፈረንጆቹ ጥቅምት 2020 ከሰጠው 114 ሚሊዮን ዶላር በእጥፍ ይበልጣል።
"ይህ ክፍያ እንደሚያሳየው ሊከሰቱ ስለሚችሉ የደህንነት ህግ ጥሰቶች ትክክለኛ መረጃ ለሚያደርሱ መረጃ አሽሏኪዎች ትልቅ ማበረታቻ መዘጋጀቱን ነው" ብሏል።
ለመረጃ አፈትላኪዎች የሚከፈለው ክፍያ የሚከናወነው በም/ቤት በተቋቋመው "የኢንቨስተር ጥበቃ ፈንድ" መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
በቁጥጥር ስር የሚውለው ገንዘብ ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ በሚሆንበት ጊዜ ለመረጃ ጠቋሚዎች ከተሰበሰበው ገንዘብ ከ10 በመቶ እስከ 30 በመቶ የሚሆን ገንዘብ ይከፈላል ተብሏል።