የሩሲያ ስትራቴጂክ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች በአሜሪካ ድንበር መብረራቸው ተገለጸ
የጦር አውሮፕላኖቹ በአሜሪካ እና ካናዳ ድንበር በሆነችው አላስካ አካባቢ ታይተዋል ተብሏል
አውሮፕላኖቹ ዓለም አቀፍ የዐየር ክልችን ተከትለው እንደበረሩ ተገልጿል
የሩሲያ ስትራቴጂክ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች በአሜሪካ ድንበር መብረራቸው ተገለጸ፡፡
ቱ-95ኤምሲ የተሰኙ ስትራቴጂክ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች በአሜሪካ ድንበር አቅራቢያ መብረራቸው የብዙዎችን ትኩረት ስቧል፡፡
ያለማቋረጥ ለዘጠኝ ሰዓታት መብረር ይችላሉ የሚባሉት እነዚህ ዘመናዊ የጦር አውሮፕላኖች አላስካ በምትሰኘው የአሜሪካ እና ካናዳ ድንበር አቅራቢያ በረዋል ተብሏል፡፡
የሰሜን አሜሪካ አየር መቆጣጠሪያ እዝ አራት የሩሲያ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች የአላስካ አየር ክልልን ጥሰው ገብተዋል ያለ ሲሆን የአውሮፕላኖቹን በረራ ሲከታተላቸው እንደቆየ አስታውቋል፡፡
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖቹ በአሜሪካዋ አላስካ የበረሩት ዓለም አቀፍ የበረራ መስመርን ተከትለው እንጂ የማንኛውንም ሀገር ሉዓላዊነት አልጣሱም ብሏል፡፡
ፕሬዝዳንት ፑቲን ከዓመታ በፊት በሰጡት ቃለ መጠይቅ ስትራቴጂክ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖቻችንን ወደ ቀድሞ ሶቪየት ህብረት ግዛት ወደ ሆኑ ቦታዎች እንልካለን ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
በ26 ዓመቷ የ22 ልጆች እናት የሆነችው ሩሲያዊት
ቱ-95 የተሰኘው የሩሲያ ሰራሽ ቦምብ ጣይ አውሮፕላን አራት ሞተር የተገጠመለት ዘመናዊ የውጊያ አውሮፕላን ሲሆን አሜሪካ ቢ-52 የተሰኘውን ተመሳሳይ የውጊያ አውሮፕላን አላት፡፡
የበረዶ ግግር የማይጠፋባት አላስካ ግዛት ከ65 ዓመት በፊት ወደ አሜሪካ የተካለለች ሲሆን አሜሪካን ከካናዳ እና ሩሲያ ጋር ታዋስናለች፡፡
ከአንድ ሚሊዮን በታች ህዝብ የሚኖርባት አላስካ ግዛት በደሴቶች እና ውሃማ አካላት የተሞላች ቁልፍ አካባቢ ስትሆን አሜሪካ ወደ አውሮፓ እና እስያ በቀላሉ እንድትገናኝ ለማድረግ አመቺም ናት፡፡