ሎስ አንጀለስ አደገኛው ንፋስ ከመመለሱ በፊት ሰደድ እሳቱን ለማስቆም እየተጣደፈች ነው
በአሜሪካ ታሪክ ከባድ ሊሆን ይችላል በተባለው የተፈጥሮ አደጋ ቢያንስ 24 ሰዎች ሲሞቱ እና 100ሺ ሰዎች ደግሞ ተፈናቅለዋል
ባለስልጣናት በእሳቱ እና በመርዛማው ጭስ ምክንያት 10 ሚሊዮን ገደማ የሚሆነው የሎስ አንጀለስ ካውንቲ ህዝብ ለቆ እንዲወጣ ሊታዘዝ ይችላሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል
የእሳት አደጋ ሰራተኞች አደገኛው ንፋሱ በድጋሚ ከመከሰቱ በፊት እስከ እሁድ ድረስ ለተከታታይ ስድስት ቀናት በሁለት በኩል እየነደዱ ያሉትን አሳቶች ለማስቆም እየተጣደፉ ናቸው።
የካሊፎርኒያ ገዥ ጋቪን ኒውሶም በአሜሪካ ታሪክ ከባድ ነው ሲሉ በገለጹት የተፈጥሮ አደጋ ቢያንስ 24 ሰዎች ሲሞቱ እና 100ሺ ሰዎች ደግሞ ተፈናቅለዋል።
እሳቱ የደሃ፣ የሀብታምና የታዋቂ ሰዎችን ቤት ሳይለይ ወደ አመድነት የቀየረ ሲሆን ቦታውንም አውድሞታል። ባለስልጣናት እንደገለጹት ከሆነ 12 ሺ ህንጻወች ጉዳት ደርሶባቸዋል አያለም ወድመዋል።
"ሎስ አንጀለስ ካውንቲ ካባድ የተባለ ሽብር እና ጭንቀት አሳልፋለች" ሲሉ የሎስ አንጀለስ ካውንቲ ተቆጣጣሪ ሊንድሴይ ሆርቫዝ።
የእሳት አደጋ ሰራተኞች በሄሊኮፕተር ውሃ ከፓሲፊክ ውቅያኖስ እየቀዱ፣ ውሃ እና ሪተርዳንት ወይም እሳት የሚያዘገይ ሲረጩ ሌሎች ደግሞ የእጅ መሳሪያዎችን በመጠቀም ወደ ቤንትውድ እና ወደ ሌሎች ህዝብ ወደሚበዛባቸው ቦታዎች እየተስፋፋ ያለውን የፖሊሳደስ እሳት ለመገደብ እየተሯሯጡ ይገኛሉ።
በከተማዋ ምዕራብ በኩል የተቀሰቀሰው ሰደድ አሳት 96 ስኩየር ኪሎሜትር ያቀጣለ ሲሆን 13 በመቶ በቁጥጥር ስር ውሏል። ከሎስ አንጀለስ ምስራቅ በኩል የተነሳው የኢቶን እሳት ደግሞ ከማንሀተን ጋር የሚስተካከል 57 ስኩየር ኪሎሜትር ቦታ ያወደመ ሲሆን የእሳት አደጋ ሰራተኞች የመቆጣጠር አቅማቸውን ቀደም ሲል ከነበረው 15 በመቶ ወደ 27 በመቶ ከፍ ማድረግ ችለዋል ተብሏል።
ከከተማዋ በሰሜን የሚገኘው የሁርስት እሳት 89 በመቶ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ሌሎች ቦታዎችን ያቃጠሉ ሌሎች እሳቶች ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የካሊፎርኒያ የደን እና የእሳት አደጋ መከላከል ሪፖርት አድርጓል።
ነፋሱን ሲያባብስ የነበረው የሁሪካን ጉልበት አግኝቶ የነበረው የሳንታ አና ንፋስ ረገብ ማለቱን ተከትሎ የእሳት አደጋ ሰራተኞች አሁን ጊዜያው እረፍት አግኝተዋል። ከበረሀማ ደሴቶች የተነሱት ደረቅ ንፋሶች የእሳቱን ፍም እሳቱ ከደረሰበት ቦታ ወደፊት ከ 3 ኪሎሜትር ድረስ አድርሰውታል።
ነገርግን ከሚያዝያ ጀምሮ ዝናብ ባልደረሰባቸው ቦታዎች የሳንታ አና ንፋስ ከ 80-112 ኪሎሜትር በሰአት እንደሚፈጥን የናሽናል ዌዘር ሰርቪስ ትንበያ ያሳያል።
ባለስልጣናት በእሳቱ እና በመርዛማው ጭስ ምክንያት 10 ሚሊዮን ገደማ የሚሆነው የሎስ አንጀለስ ካውንቲ ህዝብ ለቆ እንዲወጣ ሊታዘዝ ይችላሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል።