አሜሪካ ከዚህ በፊት በግብጽ ባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት ወታደራዊ እርዳታዋን ቀንሳ ነበር
አሜሪካ ለግብጽ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ እርዳታ ሰጠች፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ለግብጽ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ሰጥታለች፡፡
አሜሪካ ቁልፍ አጋር ለምትላቸው ለተወሰኑ ዓለማችን ሀገራት የቀጥታ ገንዘብ ድጋፍ የምታደርግ ሲሆን ግብጽ ከነዚህ መካከል አንዷ ናት፡፡
አሜሪካ ግብጽን ባለፉት ዓመታት የከፋ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ትፈጽማለች በሚል በገንዘብ ድጋፉ ለይ ቅናሽ ስታደርግ ቆታለች፡፡
ይሁንና ግብጽ የተወሰኑ መሻሻሎችን አሳይታለች በሚል በተያዘው ዓመት የ1 ነትብ 3 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ አክለውም ግብጽ በመካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ የአሜሪካ ዋነኛ አጋር መሆኗን ተናግረው በተለይም በእስራኤል-ሐማስ ድርድር ዙሪያ ቁልፍ ሚና እየተወጣች ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በጸጥታው ምክር ቤት በግብጽ ለቀረበባት ክስ ምላሽ ሰጠች
የፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ መንግስት ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ከ2 ሺህ 270 በላይ የፖለቲካ እስረኞችን ያሰረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 970 ያህሉ ከእስር ተለቀዋል ተብሏል፡፡
በግብጽ ጉብኘት ያደረጉት ብሊንከን በካይሮ እየተካሄደ ለው የእስራኤል- ሐማስ ድርድር በቅርቡ ወደ ስምምነት እንደሚመጡ እና በጋዛ ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት እንደሚፈረም ተስፋ እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡
ከ41 ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያ የተገደሉበት የእስራኤል ሐማስ ጦርነት አንድ ዓመት ሊሞላው ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርቶታል፡፡