ሩሲያ ከጥቅምት ወር ጀምሮ ወሳኝ በሆኑ የዩክሬን መሠረተ ልማት አውታሮች በሚሳይል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ስትሰነዝር ቆይታለች
ኢራን ለሩሲያ ድሮን በማቅረቧ ምክንያት አሜሪካ አዲስ ማእቀብ ጥላባታለች፡፡
አሜሪካ እንደገለጸችው ኢራን ለሩሲያ የምትሰጣቸው ድሮኖች በዩክሬን ውስጥ ያሉ የሰላማዊ ሰዎችን መሰረተ ልማት ለማውደም ጥቅም ላይ ውለዋል ተብሏል፡፡ በዚህ ምክንያት አሜሪካ የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላኖች አቅርቦት ላይ ላይ ያነጣጠረ አዲስ ማዕቀብ አርብ ዕለት መጣሏን አስታውቃለች፡፡
ሩሲያ ከጥቅምት ወር ጀምሮ ወሳኝ በሆኑ የዩክሬን መሠረተ ልማት አውታሮች በሚሳይል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ስትሰነዝር ቆይታለች።
የአሜሪካ የግምጃ ቤት ዲፓርትመንት የኢራን ኪዮድስ አቪዬሽን ኢንዱስትሪዎች (QAI) እና ቀላል አውሮፕላኖች ዲዛይን እና ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች በመባል በሚታወቁት ስድስት ስራ አስፈፃሚዎች እና የቦርድ አባላት ላይ ማዕቀብ ተጥሏል ብሏል።
ከፈረንጆቹ 2013 ጀምሮ በአሜሪካ ማዕቀብ ስር የሚገኘውን ኪዮድስ አቪዬሽን ኢንዱስትሪዎች ሰው አልባ አውሮፕላኖችን የመንደፍ እና የማምረት ሃላፊነት ያለው የኢራን የመከላከያ አምራች እንደሆነ ግምጃ ቤቱ ገልጿል።