የሉዊዝያና ግዛት በመማርያ ክፍል ውስጥ አስርቱ ትዕዛዛትን ለመስቀል ያወጣችው መመሪያ በፍርድ ቤት ታገደ
ግዛቷ ተማሪዎች ስነምግባርን እንዲማሩ በሚል በሁሉም የመንግሰት ትምህርት ቤቶች አስርቱን ትእዛዛት ለመስቀል መመሪያ አውጥታ ነበር
ፍርድ ቤቱ መመሪያው የተማሪዎችን የሀይማት ነጻነት ይጋፋል በሚል ከመፈጸም አግዶታል
የሉዊዝያና ግዛት በመማርያ ክፍል ውስጥ አስርቱ ትዕዛዛትን ለመስቀል ያወጣችው መመሪያ በፍርድ ቤት ታገደ።
ግዛቷ ተማሪዎች ስነምግባርን እንዲማሩ በሚል በሁሉም የመንግሰት ትምህርት ቤቶች አስርቱን ትእዛዛት ለመስቀል መመሪያ አውጥታ ነበርደ
የሉዊዝያና ግዛት የፌደራል ፍርድ ቤት አስርቱ ትዕዛዛት በግዛቱ ውስጥ ባሉ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የመማሪያ ክፍሎች ውስጥ እንዲሰቀሉ የሚያዘውን ህግ ኢ-ህገመንግስታዊ ነው ሲል እንዳይፈጸም ከለከለ፡፡
ህጉን እንዳይፈጸም የከለከለው ፍርድ ቤት ትዕዛዛቱን በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ መስቀል “አግላይ ፣ አስገዳጅ እና በህብረተሰቡ ውስጥ የሚገኙ የአንድ አምነት መገለጫዎችን አጉልቶ ለማሳየት የሚጥሩ የወግ አጥባቂ ቡድኖች ማሳያ ነው” ብሎታል፡፡
ህጻናቱ የሚከተሉትን እምነት እና አስተሳሰብ የመምረጥ መብት ሊኖራቸው ይገባል ያለው ፍርድ ቤት ይህ ህግ ነጻነታቸውን የሚጋፈ ነው ሲል ከጥር 1 ጀምሮ ተግባራዊ እንዳይሆን አግዷል፡፡
መመሪያው ተግባራዊ እንዳይሆን የታገደው አይሁዶች ፣ ኢ-አማንያን እና ሌሎች የተለየ እምነት የሚከተሉ 9 የተማሪ ወላጆች በግዛቷ ላይ ክስ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው፡፡
የአሜሪካ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ከሀይማኖት እና ከሰብአዊ መብቶች ጋር በተገናኘ በተለያዩ የመንግስት ሀላፊዎች እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች ዘንድ የፍልሚያ ሜዳ ናቸው፡፡
ከዚህ ጋር በተገናኘ በየግዛቱ የሚወጡ ህጎች እና መመሪያዎችም ብዙ ጊዜ ከፍ ያለ ውዝግብ እንደሚገጥማቸው ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የሪፐብሊካን የሉዊዝያና ዋና አቃቤህግ ሊዝ መሪል ፍርድ ቤቱ የወሰነውን ውሳኔ እንደሚቃወሙ እና በጉዳዩ ላይ ይግባኝ እንደሚጠይቁ ተናግረዋል፡፡
ተመራጩ ፕሬዝዳት ዶናልድ ትራምፕ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የጸሎት ስነስርአት ተግባረዊ እንዲደረግ ከሚፈልጉ ሰዎች መካከል ናቸው
የሪፐብሊካኑ የግዛቷ አስተዳዳሪ ጄፍ ላንድሪ ባሳለፍነው አመት ሰኔ በግዛቷ የመንግስት ትምህርት ቤቶች አስርቱ ትዕዛዛት እንዲሰቀሉ የሚጠይቀውን ረቂቅ ህግ 71 ላይ ፊርማቸውን ማኖራቸውን ተከትሎ ሉዊዝያና ትእዛዛቱን የሰቀለች የመጀመርያዋ የአሜሪካ ግዛት አድርጓት ነበር፡፡
ህጉ ትእዘዛቱ ጎላ ብለው በሚታዩበት አጻጻፍ የሰፈሩባቸው 11 በ 4 ኢንች የሆነ ፍሬም ወይም ፖስተር በክፍሉ ማዕከላዊ ስፍራ ላይ እንዲሰቀል ያዛል፡፡
ተማሪዎች ከመጸሀፍ ቅዱስ ትዕዛዛት ስነምግባር እና ግብረገብን እንዲማሩ እንዲሁም ከእኩዮቻቸው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት ጤናማ ለማድረግ ይረዳል በሚል ነበር ህጉ ወጥቶ የነበረው፡፡