የአሜሪካ ህግ አውጭዎች ታይዋን ገብተዋል፤ የአሜሪከ እና ቻይና ፍጥጫም ቀጥሏል
በፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት የተቆጣችው ቻይና በፔሎሲም ላይ ማእቀብ ጥላለች
ከፔሎሲ ጉብኝት በኋላ ከፍተኛ የአሜሪካ የልኡካን ቡድን ታይዋን ገብቷል
የአሜሪካ ህግ አውጭዎች ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት በዛሬው እለት ታይዋን ገብተዋል፡፡
የህግ አውጭዎቹ ጉብኝት፤ የአሜሪካ አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ በታይዋን ካደረጉት ጉብኝት ቀጥሎ ታይዋንን የጎበኘ የከፍተኛ ባለስልጣናት የልኡክ ቡደን መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የፔሎሲ የታየዋን ጉብኝት ታይዋንን የግዛቷ አካል አድርጋ የምታያትን ቻይናን ክፉኛ ማስቆጣቱ ይታወሳል፤ ሁለቱ ኃያላን ሀገራትም ወታደራዊ ፍጥጫ ውስጥ ውስጥ ሊገቡ ችለዋል፡፡
የልኡክ ቡድኑ ከታይን ፕሬዝደንት ጻይ ኢንግ ዌን ጋር ይገናኛሉ፡፡
በታይፔ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የልዑካን ቡድኑ በሴናተር ኢድ ማርኬይ እየተመራ የሚያካሂደው የኢንዶ-ፓሲፊክ ክልል ትልቅ ጉብኝት አካል እንደሆነ ገልጿል።
የታይዋን ፕሬዚዳንታዊ ጽህፈት ቤት ቡድኑ ሰኞ ማለዳ ላይ ከፕሬዝዳንት ጻይ ኢንግ ዌንግ ጋር እንደሚገናኝ ተናግሯል።
"በተለይ ቻይና በታይዋን ባህር ዳርቻ እና በአካባቢው ወታደራዊ ልምምድ በማድረግ ውጥረትን እያሳደገች ባለችበት ወቅት ማርኬ ታይዋንን መጎብኘት የልዑካን ቡድን መሪነት በድጋሚ የአሜሪካ ኮንግረስ ለታይዋን ያለውን ጽኑ ድጋፍ ያሳያል" ብሏል።
የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው ፎቶ የልኡካን ቡድኑ አባላት በአሜሪካ የአየር ሀይል ማመላለሻ ጄት ወደ ታይዋን አየር ማረፊያ ሲደርሱ ያሳያል፡፡
በፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት የተቆጣችው ቻይና፤ በታይዋን ዙሪያ ወደራዊ ልምምድ አድርጋለች፤ በፔሎሲም ላይ ማእቀብ ጥላለች፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቻይና ከአሜሪካ ጋር የነበራትን ወታደራዊ ትብብር ማቋረጧን ማስታወቋ ይታወሳል፡፡