ታይዋን፤ አሜሪካ በታይዋን ባህር ዳርቻ አካባቢን ደህንነት ለመስጠበቅ ለወሰደቻቸው እርምጃዎች አመሰገነች
ታይዋን፤ የቻይና “ወታደራዊና የኢኮኖሚ ዛቻ የዓለም አቀፉን የዲሞክራሲ ካምፕ አንድነት የበለጠ አጠናክሯል” ብላለች
በምስራቅ ታይዋን አከባቢ የተፈጠረው ውጥረት ወዳልተፈለገ የጦር መማዘዝ እንዳያመራ ተሰግቷል
የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ አሜሪካ በታይዋን ባህር ዳርቻ እና በአካባቢው ያለውን ደህንነትና ሰላም ለመስጠበቅ ለወሰደቻቸው "ተጨባጭ እርምጃዎች" አመሰገነ።
የፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ተከትሎ ፤ ቻይና በታይዋን ላይ ጥቃት ልትሰነዝር ትችላለች በሚል በምስራቅ ታይዋን አከባቢ ከፍተኛ ውጥረት እንደነገሰ የሚታወቅ ነው።
በታይዋን ላይ ለሚቃጣ ማንኛውም ጥቃት ካለ ከታይዋን ጎን ነኝ የምትለው አሜሪካ ለታይዋን አስፈላጊ የሚባለውን ድጋፍ እንደምታደርግ ይታመናል።
ለዚህም የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ አሜሪካ በታይዋን ባህር ዳርቻ ያለውን ደህንነት ለመስጠበቅ ለወሰደቻቸው "ተጨባጭ እርምጃዎች" ማማስገኑነወ ሮይተርስ ዘግቧል።
የሚኒስቴሩ መግለጫ አሜሪካ የወሰደቻቸው “ተጨባጭ እርምጃዎች” በተመለከተ ግን ያለው ነገር የለም።
ሚኒስቴሩ የቻይና "ወታደራዊ እና የኢኮኖሚ ዛቻ የዓለም አቀፉን የዲሞክራሲ ካምፕ አንድነት እና ጥንካሬ የበለጠ አጠናክሯል” ብሏል።
የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆሴፍ ው ከቀናት በፊት በሰጡት መግለጫ፤ አሜሪካን ጨምሮ የታይዋን አጋሮች ለቤጂንግ ድርጊት የሰጡት ምላሽ "የተቀረው ዓለም አቋም ዴሞክራሲ ለአምባገነንነት ዛቻ እንደማይንበረከክ ለዓለም ግልጽ መልእክት ያስተላለፈ ነው" ማለታቸው አይዘነጋም፡፡
ቤጂንግ፤ የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን የሚጎበኙ ከሆነ ጦሯ “ዝም ብሎ እንደማይቀመጥ” ስታስጠነቅቅ መቆየቷ የሚታወስ ነው፡፡
እናም በምስራቅ ታይዋን አከባቢ የተፈጸረው ውጥረት ወዳልተፈለገ የጦር መማዘዝ እንዳያመራ ተሰግቷል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ፤ ታይዋንን ከቻይና ወረራ ለመጠበቅ ኃይል ልትጠቀም እንደምትችል ፕሬዝዳንት ጆ-ባይደን ከወራት በፊት በጃፓን ጉብኝታቸው መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡
ጆ-ባይደን “ቻይና ታይዋንን በተመለከተ ኃይል የምትጠቀም ከሆነ እኛም መጠቀማችን አይቀርም” ነበር ያሉት፡፡