የሪፐብሊካኑ መሪ ኬቨን ማካርቲ በተደረገው 15ኛው ዙር ድምጽ በአራተኛው ቀን ከበርካታ ድርድር እና ድምጽ አሰጣጥ በኋላ መጨረሻ ላይ አሸንፈዋል
የአሜሪካ ፓርላማ ከ15ኛ ጊዜ ሙከራ በኋላ አዲስ አፈ-ጉባኤ መረጠ።
የሪፐብሊካኑ መሪ ኬቨን ማካርቲ በተደረገው 15ኛው ዙር ድምጽ በአራተኛው ቀን ከበርካታ ድርድር እና ድምጽ አሰጣጥ በኋላ መጨረሻ ላይ አሸንፈዋል።
ይህም ከሀገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ ታይቶ አይታወቅም ተብሏል።
- የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት አፈ ጉባኤ የመምረጥ ሂደት ለ11ኛ ጊዜ ከሸፈ
- 90 በመቶ አሜሪካዊያን በሀገራቸው የፖለቲካ ግጭት ይከሰታል ብለው እንደሚያምኑ ጥናት አመለከተ
በአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታሪክ ከፈረንጆቹ 1789 ጀምሮ 127 የአፈ-ጉባኤ ምርጫዎች ተካሂደዋል።
በዘመናዊው ዘመን አንድ ተመራጭ አፈ-ጉባኤ አብዛኞቹ የምክር ቤቱ አባላት ድምጽ መስጠት አለባቸው።
ይህም አፈ-ጉባኤ ለመሆን ከተገኙት 435 አባላት 218ቱ ድምጽ መስጠት አለባቸው ማለት ነው።
አፈ-ጉባኤ እስካልተመረጠ ድረስ የኮንግረስ አባላት ቃለ-መሀላ ፈጽመው ስራቸውን መጀመር አይችሉም ነው የተባለው።
በአሜሪካ የእርስ በርስ ጦርነት ጊዜ 13 የምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ምርጫ የተካሄደ ሲሆን፤ በድህረ እርስ በርስ ጦርነት ወቅት ደግሞ በፈረንጆቹ 1923 ዘጠኝ ጊዜ ተካሂዷል።
አዲሱ አፈ-ጉባኤን ኬቨን ማካርቲ 216 ድምጾችንን በማግኘት ነው አሸናፊ የሆኑት።
ካሊፎርኒያን ወክለው ለአሜሪካ ህግ አውጪ ምክር ቤት በአባልነት የተመረጡት ማካርቲ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀንደኛ ደጋፊ እንደሆኑ ይነገራል።
አዲሱ አፈ ጉባኤ ማካርቲ የወቅቱ የአሞሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን የሰጡትን የጦር መሳሪያ እና ገንዘብ ድጋፍ ኦዲት እንዲደረግ ማድረግ፣ በቤተሰባቸው ላይ ምርመራ እንዲደረግ እንደሚያደርጉ ከዚህ በፊት ተናግረው ነበር።
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በምርመራው ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ከስልጣናቸው ሊነሱ እንደሚችሉም እጩ አፈ ጉባኤው ከዚህ በፊት ከብዙሀን መገናኛዎች ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ላይ ጠቅሰውም ነበር።