ይህች ድሮን እስከ 24 ደቂቃ መብረር የምትችል ሲሆን በተለይም አውዳሚ የሆኑ ከባድ መሳሪያ ሁኔታዎችን ለመለየት ታገለግላለች ተብሏል
እያንዳንዱ ሰው በኪሱ ሊይዛት የምትችለው ድሮን
አሜሪካ ማንኛውም ወታደር በኪሱ ሊይዛት የሚችላት አነስተኛ ድሮን ወይም ሰው አልባ አውሮፕላን ሰርታለች፡፡
ሀገሪቱ በ2019 ጦሯን ከአፍጋኒስታን ከማስወጣቷ በፊት በካቡል እና አካባቢው በነበሩ ወታደራዊ የጦር ሰፈሮቿ ላይ ባሉ ወታደሮች ላይ ለሙከራ ላይ አውላው ነበር፡፡
ይህ ሙከራ አድጎ አሁን ላይ በኒዮርክ ያሉ የሐገሪቱ ብሔራዊ ጦር አባላት እንዲታጠቁት ማድረጓን ኒዮርክፖስት ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ይህች አነስተኛ ድሮን በተለይም በቅርብ ርቀት ላይ ያሉ አውዳሚ እና ከባድ የጦር መሳሪያዎች፣ የእሳት አደጋዎች እና ሌሎች ክስተቶችን ለመረዳት ትውላለች ተብሏል፡፡
በኒዮርክ ከተማ ያለው ብሄራዊ ጠባቂ ጦር ይህችን አነስተኛ ድሮን ታጥቀው ልምምድ እያደረጉባት ነው የተባለ ሲሆን ከትንሽ ጊዟ በኋላ ለ7 ሺህ የፖሊስ አባላት እንደሚታጠቁት በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ይህች ድሮን 24 ደቂቃ የመብረር ብቃት እና አነስተኛ ቁሳቁሶችን ይዛ የመጓዝ ብቃት አላት የተባለ ሲሆን ልዩ ኦፕሬሽኖችን ለማከናወን ታስችላለች ተብሏል፡፡
ሩሲያ እና ቻይና በጋራ ድሮን ማምረት መጀመራቸው ተነገረ
በኪስ ውስጥ ትያዛለች የተባለችው ድሮኗ የክስተቶችን ሁኔታ በቀጥታ ወይም ላይቭ ማስተላለፍ እንደምትችልም ተገልጿል፡፡
ወታደሮች ልዩ ኦፕሬሽኖችን ለማካሄድ በቦታዎቹ ላይ ልዩ ቅኝት ለማድረግ እና በወታደሮች ላይ የሚደርስን ጉዳት ለመቀነስ ጥቅም ላይ ትውላለችም ተብሏል፡፡
አዲሷ ድሮን በቀላሉ መታየት የማትችል መሆኗ ልዩ ወታደራዊ ተልዕኮዎችን ለመፈጸም ትውላለች የተባለ ሲሆን ወታደሮች ግን ድሮኗ ለመያዝ ምቹ ብትሆንም ባትሪ ቶሎ ልትጨርስ እንደምትችል ስጋታቸውን ተናግረዋል፡፡