ፖለቲካ
አሜሪካ በሩሲያ የታሰረውን ጋዜጠኛ ለማስፈታት 'የፈጠራ መፍትሄዎች' እያሰበች ነው ተባለ
ሁለቱ ሀገራት እንደኛቸው የሌላኛቸውን ዲፕሎማቶች በማባረር ዲፕሎማሲያዊ ውጥረቱ እንዲነግስ አድርገዋል
የአሜሪካ እና ሩሲያ የዩክሬኑ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ከፍተኛ መፋጠጥ ውሰጥ መግባታቸው ይታወሳል
አሜሪካ በስለላ ወንጀል ተጠርጥሮ በሩሲያ ታስሮ የሚገኘውን የወልስትሪት ጋዜጣ ጋዜጠኛ የሆነውን ኢቫን ገርሽኮቪች እንዲፈታ ለማድረግ ጥረት እያደረች መሆኑ ተገልጿል።
አሜሪካ በእስረኛ ልውውጥ ጋዜጠኛውን ለማስፈታት እጩ እየፈለገች ነው ሲል የሩሲያው አርቲ ዘግቧል።
ዋሽንግተን በአሁኑ ጊዜ ምንም የሩሲያ “ሰላዮች” በእጇ የለችም ሲል ጋዜጣው ገልጿል፣ እና ገርሽኮቪች ከቀረበባቸው የስለላ ክስ አንፃር፣ ሞስኮ በሌሎች እስረኞች ጋር የሚደረገውን መለዋወጥ እኩልነት የጎደለው አድርጋ ልትወስደው ትችላለች ብሏል ጋዜጣው።
አንድ ከፍተኛ የዋይት ሀውስ ባለስልጣን እንደተናገሩት ዋሽንግተን የገርሽኮቪች ርክክብን ለማስጠበቅ በ2020 በሩሲያ ውስጥ በስለላ ወንጀል ተከሶ ከነበረው ከፖል ዌላን ጭምር እንዲፈቱ መላ እየፈለገች ነው።
የአሜሪካ እና ሩሲያ የዩክሬኑ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ከፍተኛ መፋጠጥ ውሰጥ መግባታቸው ይታወሳል።
ሁለቱ ሀገራት እንደኛቸው የሌላኛቸውን ዲፕሎማቶች በማባረር ዲፕሎማሲያዊ ውጥረቱ እንዲነግስ አድርገዋል።
አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን ሀገራት ከሩሲያ ጋር ጦርነት የገጠመችውን ዩክሬንን በመርዳት ላይ ናቸው።