ሩሲያ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንትነትን ተረከበች
በሩሲያ ፕሬዝዳንትነት የተበሳጨችው ዩክሬን “ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ በጥፊ እንደመምታት ነው” ብላለች
ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ከጀመረች ወዲህ የፀጥታው ም/ቤት ፕሬዝዳንት ስትሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ነው
ሩሲያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የሚያዝያ ወር ፕሬዳንት ስፍራን ተረክባለች።
ዩክሬን ለሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት የወሩ ፐሬዝዳንትነት ስፍራ እንዳይሰጣት ለማድረግ በርካታ ጥረቶችን ብታደርግም ሳይሳካ ቀርቷል ነው የተባለው።
ሩሲያ ኃላፊነቱን መረከቧን ተከትሎ በተመድ የሩሲያ አምባሳደር ቫሲሊይ ናቤንዚያ፤ ሞስኮ በፕሬዝዳንትነት ጊዜወ የጦር መሳሪያ ቁጥጥርን ጨምሮ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ክርክሮችን እደምታካሂድ አስታውቀዋል።
በተጨማሪም የአንድ ሀገር የበላይነትን ስለሚያስቀረው አዲሱ የዓለም ስርዓት ላይ ውይይቶች እንደሚካሄዱም ገልጸዋል።
የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዘዳንትንት በሩሲያ መያዝ ያስደገጣት ዩክሬን በበኩሏ፤ “የወሩ ምርጥ ቀልድ ነው” በማለት አጣጥላለች።
የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሜትሪ ኩሌባ፤ “ሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዘዳንት መሆን በዓለም የደህንነት ስርዓት ውስጥ የዓለም የፀጥታ እና የደህንነት ስርዓት ውስጥ የሆነ ችግር ያሳያል” ብለዋል።
“ሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዘዳንት መሆን ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ በጥፊ እንደመምታት ነው” ሲሉም ሁኔታውን ገልጸውታል።
የተባሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አምስት ቋሚ እና 10 ተለዋዋጭ በድምሩ 15 አባላት ያሉት ሲሆን፤ ሁሉም አባላት የምክር ቤቱን የፕሬዝዳንትነት ስፍራ በየወሩ እየተቀባበሉ ይመራሉ።
ሩሲያ ለመጨረሻ ጊዜ የፀጥታው ምክር ቤት የሆነችው በፈረንጆቹ የካትቲ ወር 2022 ላይ ነበር።