የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን አሳፍሮ ሲበር የነበረው አውሮፕላን ተመልሶ ለማረፍ ተገደደ
የአሜሪካ ባለስልጣናት እንደገጹት አውሮፕላን ኮክፒት ውስጥ ዊንድሺልድ ላይ በተፈጠረ መሰንጠቅ ምክንያት አውሮፕላኑ 90 ደቂቃ ከተጓዘ በኋላ ተመልሶ ለማረፍ ተገዷል
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/14/243-105323-img-20250214-095258-838_700x400.jpg)
አሜሪካ በቅርቡ የ67 ሰዎች የቀጠፈውን የአሜሪካ ጦር ሄሊክፕተርና የአውሮፕላን ግጭት ጨምሮ ሶስት የአር አደጋ አጋጥመዋታል
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን አሳፍሮ ሲበር የነበረው አውሮፕላን በቴክኒክ ችግር ተመልሶ ለማረፍ ተገደደ።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮን አሳፍሮ ወደ ጀርመን ሙኒክ ሲጓዝ የነበረው የአሜሪካ አየር ኃይል አውሮፕላን የቴክኒክ ችግር ካጋጠመው በኋላ ወደ ዋሽንግተን ለመመለስ መገደዱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ታሚ ብሩስ ተናግረዋል።
"ሚኒስትሩ ወደ ጀርመንና መካከለኛው ምስራቅ ለመጓዝ አስበው ነበር" ብለዋል ብሩስ ባወጡት መግለጫ።
ሩቢዮ በጀርመን ሙኒክ ከሚካሄደው የጸጥታ ስብሰባ ጎን ለጎን ሊካሄድ በታሰበው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንትና የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ስብሰባ ላይ መገኘት ስለመቻላቸው ግልጽ አልሆነም።
የአሜሪካ ባለስልጣናት እንደገለጹት ከሲ-32 ወደ ቦይንግ 757 በተቀየረው ቦይንግ አውሮፕላን ኮክፒት ውስጥ ከሚገኘው የንፋስ መካከለያ ወይም ዊንድሺልድ ላይ በተፈጠረ መሰንጠቅ ምክንያት አውሮፕላኑ 90 ደቂቃ ከተጓዘ በኋላ ተመልሶ ለማረፍ ተገዷል።
ሩቢዮን ያሳፈረው አውሮፕላኑ ከዋና ከተማዋ ዳርቻ በሚገኘው በጆይንት ቤዝ አንድሬውስ በሰላም ማረፉን ሮይተርስ ዘግቧል።
አሜሪካ በቅርቡ የ67 ሰዎች የቀጠፈውን የአሜሪካ ጦር ሄሊክፕተርና የአውሮፕላን ግጭት ጨምሮ ሶስት የአር አደጋ አጋጥመዋታል።