አሜሪካ 450 ሺህ የጉጉት ወፎችን ለመግደል ማቀዷን ገለጸች
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር ለጉጉት ወፍ ግድያ በዓመት 40 ሚሊዮን ዶላር ለማውጣት በጀት ይዟል

አንድ ጉጉት ወፍን ለመግደል 3 ሺህ ዶላር ይፈጃል የተባለ ሲሆን በአጠቃላይ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ያወጣል ተብሏል
አሜሪካ 450 ሺህ የጉጉት ወፎችን ለመግደል ማቀዷን ገለጸች
የዓለማችን ቁጥር አንድ ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ 450 ሺህ ጉጉት የተሰኙ ወፎችን ለመግደል ማቀዷ ተገልጿል፡፡
ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው ከሆነ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳድር በመጠኑ ለየት ያለ አፈጣጠር ያለው ጉጉት ተብሎ የሚጠራውን ወፍ የመግደል ዘመቻ አቅዷል፡፡
ለዚህ ዘመቻ በዓመት 40 ሚሊዮን ዶላር በጀት ያስፈልጋል የተባለ ሲሆን በአማካኝ ለአንድ ጉጉት ሶስት ሺህ ዶላር ወጪ ይደረጋል፡፡
ሀገሪቱ በአጠቃላይ በቀጣዮቹ 30 ዓመታት በተለይም ከአሜሪካ ውጪ የሚመጡ የጉጉት መንጋዎችን የመግደል እቅድ አስቀምጣለች፡፡
ከፍ ያለ መጠን ያለው ጉጉት ወፍ ብዙ አይነት ዝርያዎች ያሉት ሲሆን ከውጭ ሀገራት ወደ አሜሪካ የሚገባው የጉጉት ዝርያ ከዚህ በፊት በሀገር ውስጥ ያለውን ዝርያ እየዋጠው ነው ተብሏል፡፡
የጉጉት መንጋው የሚገኝበት የካሊፎርኒያ ግዛት ምክር ቤት አባላት ግን የዶናልድ ትራምፕን ውሳኔ ተቃውመዋል፡፡
አባላቱ የጉጉት ወፎችን ለመግደል ከፍተኛ ወጪ፣ አልሞ ተኳሽ የሚፈልግ እና ሌሎች የስነ ህይወት ጉዳት የሚያደርስ ነው በሚል እቅዱን እንደተቃወሙት ተገልጿል፡፡
የአሜሪካ አሳ እና የዱር እንስሳት የተሰኘው ተቋም ይህን እቅድ እንዲያስፈጽም ሀላፊነት የተሰጠው ሲሆን በዚህ ዓመት ብቻ 2 ሺህ 700 የጉጉት ወፎች ይገደላሉ ተብሏል፡፡