አሜሪካ ለ20 ከተሞች የ53 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባች
ለአለም የከባቢ አየር ብክለት 3/4ውን ድርሻ የሚይዙት ከተሞች መሆናቸው ይገለጻል
ኃላፊዋ እንደገለጹት ድጋፉ የከተሞቹን የአየር ንብረት ለውጥ ችግር የመቀነስ ጥሪታቸውን ለማገዝ የሚውል ነው
አሜሪካ ለ20 ከተሞች የ53 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባች።
አሜሪካ በዩኤስአይዲ በኩል ኃላፊ ሳማንታ ፖወር በትናንትናው እለት በታዳጊ ሀገራት ለሚገኙ 20 ከተሞች የ53 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።
ኃላፊዋ እንደገለጹት ድጋፉ የከተሞቹን የአየር ንብረት ለውጥ ችግር የመቀነስ ጥሪታቸውን ለማገዝ የሚውል ነው።
ሳማንታ ፖወር ታዳሽ ያልሆነ የኃይል ምንጭ መጠቀም ይቁም ወይስ አይቁም የሚል ድርድር እየተካሄ ባለበት የዱባዩ የኮፕ28 ስብሰባ ላይ ተካፍለዋል።
ኃላፊዋ የሚደረገው ፈንድ እንደ ኤሌክትሪክ መኪና የመሳሰሉ የካርቦን ልቀትን ለሚቀንሱ ፕሮጀክቶች ይውላል ብለዋል።
የኪሪግዝ ዋና ከተማ ቢሽክክ፣ የህንዷ ራጅኮት፣ የደቡብ አፍሪካዋ ሞምቤላ እና የሜክሲኮዎቹ ሁለት ከተሞች ከእርዳታው ተጠቃሚ ከሚሆኑት ከተሞች መካከል ናቸው ተብሏል።
ለአለም የከባቢ አየር ብክለት 3/4ውን ድርሻ የሚይዙት ከተሞች መሆናቸው ይገለጻል።
የኮፕ28 ስብሰባ 198 ሀገራት የተወከሉበት ሲሆን ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ችግር ለመቋቋም የሚያስችል እና የሚቴን ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ የሚያስችል የገንዘብ ድጋፍ ቃል ገብለዋል።