ፕሬዝዳንት ባይደን ከስልጣን እንዲነሱ የሚጠይቅ ምርምራ ሊከፈትባቸው እንደሆነ ተገለጸ
ፕሬዝዳንቱ በሙስና እና ስልጣናቸውን ያላግባብ ተጠቅመዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል
የነጩ ቤተ መንግስት ቃል አቀባይ በፕሬዝዳንቱ ላይ የቀረበውን ክስ ተችቷል
ፕሬዝዳንት ባይደን ከስልጣን እንዲነሱ የሚጠይቅ ምርምራ ሊከፈትባቸው እንደሆነ ተገለጸ፡፡
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከልጃቸው ሀንተር ባይደን ጋር በተያያዘ ስልጣን ያላግባብ ተጠቅመዋል በሚል ክስ የቀረበባቸው ሲሆን የአሜሪካ ህግ መወሰኛ ምክር ቤትም በጉዳዩ ዙሪያ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ኬቪን ማካርቲ እንዳሉት በፕሬዝዳንት ባይደን ላይ የቀረበባቸውን ከስልጣን ይነሱ ጥያቄ መቀበላቸውን እና ምክር ቤቱም የሙስና፣ ስልጣን አጠቃቀም እና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ምርመራውን ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የፕሬዝዳንት ባይደን ልጅ የሆነው ሀንተር ባይደን የአሜሪካንን ህግ በመተላለፍ የተለያዩ የቢዝነስ ስምምነቶችን አድርገዋል ይህም የሆነው በአባቱ እውቅና እና ድጋፍ ነው የሚል ክስ በተደጋጋሚ እየቀረበ ይገኛል፡፡
የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ማካርቲ እንዳሉት ፕሬዝዳንት ባይደን ከልጃቸው ጋር በተያያዘ ግልጽ የህግ ጥሰት ስለመፈጸሙ ማስረጃዎች ተገኝተዋልም ብለዋል፡፡
አሜሪካ ዩክሬን ወደ ሰላም እንድትመጣ ግፊት ልታደርግ እንደምትችል ተገለጸ
የፕሬዝዳንት ባይደን ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ ኢያን ሳምስ በበኩላቸው በፕሬዝዳንት ባይደን ላይ የቀረበውን ክስ ተችተዋል፡፡
የሪፐብሊካን ምክር ቤት አባላት ላለፉት ዘጠኝ ወራት በፕሬዝዳንት ባይደን ላይ ምርመራ ሲያደርጉ መቆየታቸውን እና መረጃ አለማግኘታቸውንም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡
ሀንተር ባይደን በፌደራል ምርመራ ስር ሆነው ጉዳያቸው እየተመረመሩ ናቸው የተባለ ሲሆን በውጭ ሀገራት ከሚያንቀሳቅሷቸው ቢዝነሶች ጋር በተያያዘ ግብር ሰውረዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ባይደንም ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ ለልጃቸው የሕግ ከለላ አድርገዋል በሚል ስልጣንን ያላግባብ ተጠቅመዋል በሚል እየተተቹ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
በአሜሪካ ህገ መንግስት መሰረት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የሙስና ምርመራ ግኝት ከተገኘባቸው እና ሌሎች ከባድ ወንጀሎችን ፈጽመው ከተገኙ በቀጥታ ከስልጣን እንዲነሱ ያስገድዳል፡፡
ፕሬዝዳንት ባይደን ከልጃቸው ጋር በተያያዘ ፈጽመውታል የተባለው ስልጣንን ያላግባብ መጠቀም ወይም ሙስና ወንጀል መፈጸማቸው ከተረጋገጠ ከስልጣን ሊነሱ ይችላሉ ተብሏል፡፡