ሲንጋፖር ፣ ስዊዘርላንድ እና አውስትራሊያ ለመሪዎቻቸው ከፍተኛ አመታዊ ደመወዝ ከሚቆርጡ ሀገራት መካከል ይጠቀሳሉ
የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ የአለም መሪዎች ቀዳሚዎቹ ቢሆኑም እንደ ሌሎች ሠራተኞች ደመወዝ የሚቀበሉ የፌዴራል ተቀጣሪዎች ናቸው።
ይህ ደሞዝ ከአብዛኛዎቹ የስራ አይነት እና መካከለኛ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት መሪዎች ጋር ሲወዳደር አነስተኛ ነው ቢባልም፤ ስልጣኑ የሚሰጠው የገንዘብ ጥቅማጥቅም በርካታ ነው፡፡
የእስያዋ ሲንጋፖር ጠቅላይ ሚንስትር 1.69 ሚሊየን ዶላር በአመት የሚያገኙ ሲሆን ሲውዘርላንድ 572 እንዲሁም አውስትራሊያ 413 ሺህ ዶላር ለመሪዎቻቸው ይከፍላሉ፡፡
በ2001 የአሜሪካ ግምጃ ቤት ለኮንግረሱ ባቀረበው ረቂቅ መሰረት በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አመታዊ ደመወዝ 400 ሺ ዶላር ነው።
ከደመወዙ በተጨማሪ ፕሬዝዳንቱ ለግል ወጪ 50ሺ፣ ለመዝናኛ 19 ሺ እና ለጉዞ ከቀረጥ ነጻ 100 ሺህ ዶላር ይመደብለታል፡፡
አዲስ የሚመረጥ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ነጩ ቤት መንግስትን ለማስዋብ እና አዳዲስ ፈርኒቸሮችን ለመግዛት ተጨማሪ 100 ሺ ዶላር ያገኛል፡፡
በስልጣን ላይ እና ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ለአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ጥበቃ የሚያደርገው የደህንነት ተቋም “ሴክሬት ሰርቪስ” በአመት በአጠቃላይ 1.9 ቢሊየን ዶላር በጀት የተመደበለት ነው፡፡
ፕሬዚዳንቱ ከቢሮ ከተሰናበተ በኋላም በስራ ላይ ከሚገኝ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመወዝ እኩል የጡረታ ክፍያ (230ሺ ዶላር) ያገኛል፡፡