የሩሲያ ቅጥረኛ ወታደሮች ከሰሞኑ ወደ ኒያሚ ማምራታቸው ይታወሳል
አሜሪካ ጦሯን ከኒጀር እንድታስወጣ ተጠየቀች፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን የተቆጣጠረው የኒጀር ወታደራዊ አመራር ከምዕራባዊን ጋር ያለውን ግንኙነት እያቋረጠ ይገኛል፡፡
ምዕራብ አፍሪካዊቷ ኒጀር መፈንቅለ መንግስቱ ከመከሰቱ በፊት የፈረንሳይ እና አሜሪካ ዋና አጋር ነበረች፡፡
በዩራኒየም ማዕድኗ የበለጸገችው ኒጀር በሀገሯ ለረጅም ዓመታት ሰፍሮ የነበረውን የፈረንሳይ ጦር ለቆ እንዲወጣ ግፊት ስታደርግ የቆየች ሲሆን ፈረንሳይም በሀገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች የነበሩ ወታደራዊ ማዘዣዎቿን ለቃ ለመውጣት ተገዳለች፡፡
አሁን ደግሞ አሜሪካ በኒጀር ያሰፈረቻቸውን አንድ ሺህ ገደማ ወታደሮች እንድታስወጣ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በሀገሪቱ መዲና ኒያሚ ሰላማዊ ሰለፍ አድርገዋል፡፡
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የአሜሪካ ጦር በመሬታችን እንዲቆይ አንፈልግም የሚሉ መልዕክቶችን የያዙ መፈክሮችን ይዘው ወደ አደባባይ ወጥተዋል፡፡
የሩሲያው ቅጥረኛ ወታደራዊ ተቋም ዋግነር አባል የሆኑ አሰልጣኞች የኒጀርን ጦር ለማሰልጠን ወደ ኒያሚ ከሰሞኑ መግባታቸው ይታወሳል፡፡
ኒጀር ከአሜሪካ ጋር ያላትን ወታደራዊ ትብብር አቋረጠች
መፈንቅለ መንግስት በማድረግ ስልጣን የተቆጠጠሩት ሌሎቹ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ቡርኪና ፋሶ እና ማሊ ከሩሲያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማጠናከር ላይ ናቸው፡፡
ኒጀርም የሁለቱን ጎረቤት ሀገራት ልምድን በውሰድ ለይ ስትሆን በአንድ በኩል ከምዕራባዊን ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ስታቋርጥ ከሩሲያ ጋር ደግሞ የበለጠ እየተባበረች ትገበኛለች፡፡
ዓለም አቀፍ ተቋማት እና ምዕራባዊን ሀገራት በሶቱ ሀገራት ላይ እርዳታዎችን ያቆሙ ሲሆን የአፍሪካ ህብረትም ከአባልነት አግዷል፡፡
ማሊ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር ደግሞ ከምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ወይም ኢኮዋስ አባልነት ራሳቸውን አግልለዋል፡፡