ፕሬዝዳንት ባይደንም ሆኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ የሩሲያን ስጋቶች ለማዳመጥ ዝግጁ አይደሉም ተብሏል
ሩሲያ ከአሜሪካ ጋር በእጅ አዙር ጦርነት ውስጥ መሆኗ ተገለጸ
ወደ ዩክሬን የሚላከው የጦር መሳሪያ መጨመር እና የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለፕሬዝዳንት ዘለንስኪጅ ያደረጉት ከፍተኛ አቀባበል አሜሪካ ከሩሲያ ጋር “የእጅ አዙር ጦርነት” ውስጥ እንዳለች ያሳያል ሲል ክሬምሊን ተናግሯል።
አሜሪካ እና ዩክሬን ለሩሲያ ጩኸት ጆሮ ዳባ ልበስ ማለታቸውን ክሬምሊን ቮልዲሚር ዘለንስኪ ወደ ዋሽንግተን ካደረጉት ታሪካዊ ጉዞ በኋላ ተናግሯል።
ጉብኝቱ ለወራት የተወጠነ ሲሆን አሜሪካ እስካሁን ለዩክሬን ያላትን ትልቅ ቁርጠኝነት በማሳየት ሚሳይሎችን እንደምትልክ አስታውቃለች።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ “እስካሁን ፕሬዝዳንት ባይደንም ሆኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ የሩሲያን ስጋቶች ለማዳመጥ ዝግጁ እንደሆኑ የሚያመለክቱ ጥቂት ቃላትን እንኳን አልተናገሩም" ብለዋል።
“ዘለንስኪ በዶንባስ ውስጥ ባሉ ከተሞች እና መንደሮች የመኖሪያ ሕንፃዎች ላይ የሚደርሰውን ድብደባ በመቃወም አንድም ቃል ሲናገሩ አልተሰማም። ምንም እውነተኛ የሰላም ጥሪዎችም አልነበሩም። ይህ የሚያሳየው አሜሪካ ከሩሲያ ጋር ቀጥተኛ ያልሆነ ጦርነት እስከ መጨረሻው የዩክሬን ጦርነት ድረስ እየታገለች እንደሆነ ነው" ብለዋል።
አሜሪካ ወደ ዩክሬን ልትልክ ቃል የገባችውን የአየር መከላከያ ዘዴን ሩሲያ ኢላማ ታደርጋለች ሲሉም ቃል አቀባይ ፔስኮቭ ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ አክለውም ምንም እንኳን አሜሪካ እና ሌሎች አጋሮች ለዩክሬን የሚቀርቡት የጦር መሣሪያ ያለማቋረጥ በክልሉን እያስፋፋና የቴክኒክ ድጋፉ ቢያድግም፤ የሩሲያ ጦር ግን ይህ ግቦቹን ከማሳካት አይከለከልም ብለዋል።
ዘለንስኪ በዋሽንግተን "የጀግና አቀባበል" የተደረገላቸው ሲሆን ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ የዩክሬኑ መሪ ከሀገራቸው ውጭ ያደረጉት የመጀመሪያው የታወቀ ጉዞ መሆኑን ናሽናል ኒውስ ዘግቧል።