አሜሪካ በሀማስ ቃል አቀባይ እና የድሮን ፕሮግራም መሪዎች ላይ ማዕቀብ ጣለች
ሚኒስቴሩ እንደገለጸው የአውሮፓ ህብረትም በተመሳሳይ ሀማስ ላይ ያነጣጠረ ማዕቀብ ጥሏል
የአል ቃሲም ብርጌድ ቃል አቀባይ አንደኛው የማዕቀቡ ሰለባ ነው ብሏል ሚኒስቴሩ
አሜሪካ በሀማስ ቃል አቀባይ እና የድሮን ፕሮግራም መሪዎች ላይ ማዕቀብ ጣለች።
አሜሪካ በሀማስ ቃል አቀባይ እና በቡድኑ የድሮን ዩኒት መሪዎች ላይ ማዕቀብ መጣሏን የአሜሪካ ገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ እንደገለጸው የአውሮፓ ህብረትም በተመሳሳይ ሀማስ ላይ ያነጣጠረ ማዕቀብ ጥሏል።
ማዕቀቡ ያነጣጠረው ሁዳይፋ ሳሚር ወይም አል ካህሉት ተብሎ በሚጠራው የኢዝ አል ዲን አል ቃሲም ብርጌድ ቃል አቀባይ ላይ ነው።
ሚኒስቴሩ እንደገለው በዚህ ማዕቀብ መቀመጫውን ሊባኖስ ያደረገው የአል ሺማሊ ዩኒት አዛዥ ዚሊያም አቡ ሽናብ እና ረዳቱ ባራ ሀሰን ፋራት እንዲሁም የአዛም የስለላ ባለስልጣን ካሊድ ሙሀመድ አዛም ኢላማ ተደርገዋል።
የሚኒስቴሩ የሽብር እና የፋይናነስ ደህንነት ኃላፊ ብሬን ኔልሰን ማዕቀቡ የተጣለው ሀማስ ተጨማሪ ጥቃት እንዳያደርስ ለማድረግ ነው ብለዋል።
ኃላፊው "የገንዘብ ሚኒስቴር ከአጋሮቻችን ጋር በመተባበር ሀማስን በየትኛውም ቦታ እናጠቃለን"ሲሉ ተናግረዋል።
ማዕቀብ የተጣለባቸው ግለሰቦች በአማሪካ ውስጥ የሚገኘው ሀብታቸው እንዲታገድ ይደረጋል ብሏል ሚኒስቴሩ።
አሜሪካ፣ ከፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ጋር እየተዋጋች ላለችው እስራኤል የገንዘብ እና የጦር መሳሪያ ድጋፍ እያደረገች ነው።