ማዕቀቦቹ በባለስልጣናት፣ በተቋማት እና አገልግሎት መስጫዎች (መርከብና አውሮፕላኖች) ላይ ያነጣጠሩ ናቸው
ሩሲያ ባለፈው አመት የካቲት ወር ላይ በዩክሬን ላይ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ መክፈቷን ካሳወቀች ወዲህ ከ11 ሺህ በላይ ማዕቀቦች ተጥለውባታል።
ይህም ከጦርነቱ በፊት የተጣሉባት ማዕቀቦች (2754) ጋር ተዳምሮ የምዕራባውያን የማዕቀብ ናዳ የወረደባት ቀዳሚዋ ሀገር አድርጓታል።
በሞስኮ ላይ ማዕቀቦችን በብዛት በመጣል አሜሪካ (1948)፣ ስዊዘርላንድ (1782) እና ካናዳ (1590) ከፊት ይሰለፋሉ።
በተጣሉባት ማዕቀቦች ብዛት ቀዳሚ የነበረችው(ከሩሲያና ዩክሬን ጦርነት በፊት) ኢራን እና ከ2011 ጀምሮ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የገባችው ሶሪያም በርካታ ማዕቀብ የተጣለባቸው ሀገራት ዝርዝር ውስጥ አሁንም አሉ።