አሜሪካ ከካቡል ከተነሳው አውሮላን ላይ በተገኘው“የሰው ቅሪት አካል” ጉዳይ ምርመራ እያደረገች ነው
ከአሜሪካ ጋር ሲሰሩ የነበሩ የአፍጋን ዜጎች ታሊባን ይበቀለናል በሚል ፍርሃት ውስጥ ናቸው
የአሜሪካ ጦር ከአፋጋኒስታን መውጣቱን ተከትሎ ታሊባን ከ20 አመት በኋላ ቤተመንግስት ገብቷል
አሜሪካ ከአፍጋኒስታን ካቡል አየርማረፊያ ከተነሳው አውሮፕላን የጎማ ቀዳዳው ውስጥ በተገኘው የሰው ቅሪት አካል ዙሪያ ምርመራ እያካሄደች መሆኑን አስታውቃለች፡፡
ወታደራዊ አውሮፕላኑ ለመነሳት እየተንደረደረ ባለበት ወቅት የተነሱ ቪዲዮች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አውሮፕላኑ ላይ ለመንጠልጠል ሲሞክሩ ታይተዋል፤የአሜሪካ ፖሊሶችም የማስጠንቀቂያ ተኩስ ተኩሰው ነበር፡፡ አውሮፕላኑ ሲነሳ ተንጠልጥለው የነበሩት ሶሰት ሰዎች አውሮፕላኑ መብረር ከጀመረ በኋላ ከአየር ላይ ወድቀው ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡
አሜሪካ ከፍጋኒስታን ወታደሮቿን ማስወጣቷን ተከትሎ ለ20 አመታት ያህል የትጥቅ ትግል ሲያደርግ የነበረው ታሊባን በአጭር ቀናት ውስጥ ቤተመንግስት መግባት ችሏል፡፡
ታሊባን የአፍጋኒስታንን ዋና ከተማ ከመቆጣጠሩ ቀደም ብሎ ሀገሪቱን ሲመሩ የነበሩት አሽራፍ ጋኒ ወደ ጎረቤት ሀገር ሸሽተዋል፡፡
ታሊባንን በአሸባሪነት ፈርጀው፣ በአፍጋኒስታን ወታደር አሰማርተው የነበሩት አሜሪካና እንግሊዝን ጨምሮ ሌሎች የምእራባውያን ሀገራት ዲፕማቶቻቸውን በልዩ ዘመቻ ከአፍጋኒስታን ሲያስወጡ ታይተዋል፡፡
የታሊባንን ካቡል መግባት ተከትሎ በካቡል ከፍተኛ ትርምስ ተከትስቷል፤በአየርመንገድም ብዙ ሰዎች ወደ ውጭ ለመውጡት በውታደራዊ አውሮፕላን ላይ ሲንጠላጠሉ ነበር፡፡ ከአሜሪካ ጋር ሲሰሩ የነበሩ የአፍጋን ዜጎች ታሊባን ይበቀለናል በሚል ፍርሃት ውስጥ ናቸው፡፡