ኃይትሀውስ የህንድ ደህንት በካናዳ እና በአሜሪካ በተፈጸሙ ሁለት የግድያ ሴራዎች ላይ ሚና አለው የሚለውን ሪፖርት በቀላሉ እንደማያየው ገልጿል
ይትሀውስ የህንድ ደህንት በካናዳ እና በአሜሪካ በተፈጸሙ ሁለት የግድያ ሴራዎች ላይ ሚና አለው የሚለውን ሪፖርት በቀላሉ እንደማያየው በትናትናው እለት ገልጿል።
የህንድ ደህንነት አገልግሎት አባል የጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ዋነኛ ተቃዋሚ የሆኑትን አሜሪካዊ ዜጋ በአሜሪካ ውስጥ ለመግደል በተደረገ ሙከራ መሳተፉን ሮይተርስ ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣን ጠቅሶ ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ ይህ የደህንነት አባል ባለፈው ሰኔ ወር በካናዳ ከተፈጸመው የሲክ አክተመቪስት ግድያ ጀርባ እጁ አለበት።
የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዋሽንግተን ፖስት ዘገባ በመረጃ ላይ ያልተደገፈ ነው ሲል አጣጥሎታል።
"በጉዳዩ ላይ በትክክለኛ መረጃ ላይ ያልተመሰረተ እና ኃላፊነት የጎደለው አስተያየት መስጠት ጥቅም የለውም" ሲሉ የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ራንዲር ጄስዋል ባወጡት መግለጫ ተናግረዋል።
የኃይትሀወስ ቃል አቀባይ ካሪን ጂን ፔሪም "ይህ ከባድ ጉዳይ ነው፤ ጉዳዩን በከፍተኛ ትኩረት ነው እንከታተለዋለን" ብለዋል።
ቃል አቀባይዋ እንዳሉት በጉዳዩ ዙሪያ ያላቸውን ስጋት ማንሳታቸውን ይቀጥላሉ።
ባለፈው ህዳር ወር የአሜሪካ ባለስልጣናት የህንድ መንግስት ባለስልጣናት የአሜሪካ እና የካናዳ ዜግነት ባለው የሲክ ተገንጣይ ጉርባትዋንት ስኝ ፓኑን ላይ የተቃጣውን የግድያ ሙከራ መርተዋል ሲሉ ከሰው ነበር።
ህንድ የግድያ ሙከራው ከእሷ ጋር መያያዙን እንደማትቀበል እና ጉዳዩን ለመመርመር ህዳር 18 የተቋቋመው ኮሜት የሚደርስበትን ግኝት ተከታትላ እርምጃ እንደምትወስድ ገልጻለች።
ፓኑን ህንድ በ2019 በጽንፈኝነት የፈረጀችው የሲክ ፎር ጀስቲስ የህግ አማካሪ ነው።