የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ከሆስፒታል መውጣታቸው ተገለጸ
ሚኒስትሩ መታመማቸውን ለባልደረቦቻቸው እና ለኃይትሀውስ ዘግይተው በመናገራቸው ምክንያት ትችት ተሰንዝሮባቸዋል
የ70 አመቱ ኦስቲን ባለፈው ታህሳስ ወር ያደረጉት ቀዶ ጥገና ችግር ስለፈጠረባቸው ባለፈው ጥር አንድ በድጋሚ ወደ ሆስፒታል ገብተው ነበር
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ከሆስፒታል መውጣታቸው ተገለጸ።
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን ከሆስፒታል መውጣታቸውን እና ስራቸውን ከርቀት እያከናወኑ መሆናቸውን ፔንታጐን አስታውቋል።
ሚኒስትሩ መታመማቸውን ለባልደረቦቻቸው እና ለኃይትሀውስ ዘግይተው በመናገራቸው ምክንያት ትችት ተሰንዝሮባቸዋል።
የ70 አመቱ ኦስቲን ባለፈው ታህሳስ ወር ያደረጉት ቀዶ ጥገና ችግር ስለፈጠረባቸው ባለፈው ጥር አንድ በድጋሚ ወደ ሆስፒታል ገብተው ነበር።
የሚኒስትሩ ዶክተሮች እንደተናገሩት ኦስቲን ሙሉ በመሉ ያገግማሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል።
በዋልተር ሬድ ናሽናል ሚሊተሪ ሜዲካል ሴንተር የሚሰሩት ዶክተር ጆን ማዶክስ እና ዶክተር ግሪጎሪ ቸስነት እንደተናገሩት ሚኒስትሩ በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን እና ጥንካሬያቸውን እየተመለሰ መሆኑን ተናግረዋል።
ዶክተሮቹ እንዳሉት ሚስትሩ ያጋጠማቸው የፕሮስቴት ካንስር ጊዜ ሳይወስድ እና በጥሩ ሁኔታ ታክሟል።
የመከላከያ ሚኒስትር በዕዝ ሰንሰለቱ ውስጥ ከፕሬዝደንቱ ቀጥሎ ያለ ቁልፍ ከሚባሉት ካቢኔቶች ውስጥ አንዱ ነው።
ኦስቲን ባለፈው ታህሳስ ወር የፕሮስቴት ካንስር ምርመራ አድርገው ነበር።
ኦስቲን ከዚሁ ህክምና ጋር በያያዘ ችግር በአዲስ አመት ዋዜማ በድጋሚ ወደ ሆስፒታል ገብተው እንደነበር ተገልጿል።
ከፍተኛ የመከላከያ ባለስልጣናት እና ኃይትሀውስ ሎይድ ሆስፒታል ገብተው ሶስት ቀን እስከሚሆናቸው ድረስ አልሰሙም።
ሎይድ የጤናቸውን ሁኔታ ህዝቡ በወቅቱ እንዲያቀው ባለማድረጋቸው ይቅርታ ጠይቀዋል።