በእስራኤል የሚገኙት ባይደን የጋዛው ፍንዳታ የተፈጸመው በታጣቂዎች ነው አሉ
በሆስፒታሉ ላይ የደረሰው ጥቃት በዌስት ባንክ እና በአረቡ አለም ቁጣን ቀስቅሷል
በሆስፒታሉ ላይ በደረሰው ጥቃት ከ500 በላይ ሰዎች የሞቱ ሲሆን ጥቃቱን በማድረስ እስራኤል እና ሀማስ እርስበእርሳቸው በመካሰስ ላይ ናቸው
በእስራኤል የሚገኙት ባይደን የጋዛው ፍንዳታ የተፈጸመው በታጣቂዎች ነው አሉ።
በእስራኤል በጉብኝት ላይ የሚገኙት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በጋዛ በሚገኘው የአል አህሊ ሆስፒታል ላይ ፍንዳታ የደረሰው በታጣቂዎች ነው ብለዋል።
በሆስፒታሉ ላይ በደረሰው ጥቃት ከ500 በላይ ሰዎች የሞቱ ሲሆን ጥቃቱን በማድረስ እስራኤል እና ሀማስ እርስበእርሳቸው በመካሰስ ላይ ናቸው።
ፕሬዝደንት ባይደን ፍንዳታው የተፈጸመው በእስራኤል ሳይሆን በሀማስ ታጣቂዎች ነው በማለት የእስራኤልን መግለጫ ደግፈዋል።
የሆስፒታሉን ጥቃት ተከትሎ ጆርዳን ከፕሬዝደንት ባይን፣ ከግብጽ እና ከፍልስጤም መሪዎች ጋር በጋዛ ጉዳይ በአማን ልታደርግ የነበረውን ስብሰባ መሰረዟን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አይመን ሳፋዲ አስታውቀዋል።
በሆስፒታሉ ላይ የደረሰው ጥቃት በዌስት ባንክ እና በአረቡ አለም ቁጣን ቀስቅሷል።
እስራኤል ድንበሯን ጥሶ ከ1300 በላይ ዜጎቿን የገደለባትን የፍልስጤሙን ታጠቂ ቡድን ሀማስን ከምድረ ገጹ ለማጥፋት እየወሰደች ያለው እርምጃ አሁንም እንደቀጠለ ነው። የሀማስ ይዞታ የሆነችውን ጋዛን በመክበብ በእግረኛ ወታደር ጥቃት ለመሰንዘር በዝግጅት ላይ ነች።