ፖለቲካ
በበርካታ ግድያዎች ላይ እጁ አለበት የተባለ የአል ሸባብ መሪ መገደሉን ሶማሊያ ገለጸች
አይማን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተፈልጎ እንዲያዝ ትዕዛዝ አውጥቶበታል።
የአሜሪካ ጦር የአፍሪካ እዝ የአየር ጥቃት መፈጸሙን የእዙ ቃል አቀባይ ገልጸዋል
በበርካታ ግድያዎች ላይ እጁ አለበት የተባለ የአል ሸባብ መሪ መገደሉን ሶማሊያ ገለጸች።
ሶማሊያ እና አሜሪካ በርካታ ግድያዎችን በማቀድ አስፈጽሟል ያሉትን ከፍተኛ የአል ሸባብ መሪ መግደላቸውን የሶማሊያ የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር አስታውቋል።
ዳውድ አዊስ በትዊተረ ገዳቸው "መአሊም አይማን...በሶማሊያ ብሔራዊ ጦር እና በአሜሪካ ድጋፍ በተደረገ የጋራ ዘመቻ መገደሉ ተረጋግጧል" ሲሉ ተናግረዋል።
ዳውድ አዊስ "አይማን በሶማሊያ እና በቅርብ ሀገራት ለተከሰቱ በርካታ ዘግናኝ ጥቃቶችን ተጠያቂ ነው" ብሏል።
የአሜሪካ ጦር የአፍሪካ እዝ የአየር ጥቃት መፈጸሙን የእዙ ቃል አቀባይ ገልጸዋል። ነገርግን ቃል አቀባዩ የአየር ጥቃቱ ኢላማውን መምታቱ ገና አልተረጋገጠም ብለዋል።
አይማን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተፈልጎ እንዲያዝ ትዕዛዝ አውጥቶበታል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አይማን ሶስት አሜሪካውያን የተገደሉበትን በ2020 በኬንያ በሚገኘው የጦር ሰፈር የተፈጸመውን ጥቃት ያቀናበረው ይህ ግለሰብ ነው ብሏል።