አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ የሚመጣውን ማንኛውንም የኒውክሌር አደጋ ለመጋፈጥ ዝግጁ ነን አሉ
አሜሪካ፤ ፒዮንጊያንግ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ከተጠቀመች ምላሹ የከፋ ይሆናል ስትል አስጠንቅቃለች
አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ ለስምንተኛ ጊዜ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ አደርገዋል
ሰሜን ኮሪያ ባለፈው ዓመት ወደ አሜሪካ ጭምር ሊደርሱ እንደሚችሉ የሚገርላቸው በርካታ ቁጥር ያላቸውን እህጉር አቋራጭ ሚሳዔሎች ባለስቲክ ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏ አይዘነጋም።
ሀገሪቱ ሰኞ እለት ሁለት ሚሳዔሎችን ወደ ፓሲፊክ ውቅያኖስ በማስወንጨፍ የቀጣነውን ሀገራት ስጋት ውስጥ ከምክተቷ በዘለለ በዛሬው እለት አራት የክሩዝ ሚሳዔሎችን ማስወንጨፏንም አስታውቃለች።
በዚህም በኮሪያ ልሳነ ምድር እየተጋጋለ የመጣውን ውጥረት ያሰጋቸው አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ከፒዮንጊያን ሊመጣ የሚችለውን አደጋ ለመመከት የሚያስችላቸውን የኒውክሌር ጥቃት የጋራ ልምምድ እያካሄዱ መሆናቸው የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የሀገራቱ ባለስልጣናት ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ልትጠቀም ትችላለች የሚል ማስጠንቀቂያ ከሰጡበት ከ2017 አንስቶ፤ አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ መሰል የጋራ መታደራዊ ልምምድ ሲያደረጉ መቆየታቸው ይታወቃል።
የአሁን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ለስምነተኛ ጊዜእየተደረገ ያለ መሆኑም ነው የተነገረው።
መከላከያ ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ የሚመጣውን ማንኛውንም የኒውክሌር አደጋ ለመጋፈጥ ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል።
ሀገራቱ ተልዕኳቸውን ለመወጣት የስለላ ልውውጥን፣ የቀውስ ምክክርን እና የጋራ ወታደራዊ እቅድ ለማውጣትም ከስምምነት ደርሰዋል።
የፔንታጎን መግለጫ " የቅርቡ የአሜሪካ እና የደቡብ ኮሪያ ልዑካን ውይይት በኮሪያ ልሳነ ምድር ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን እና ለሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ አጠቃቀም ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ አማራጮች ላይ ያተኮረ ነበር"ብሏል።
ሁለቱ የልዑካን ቡድን ከደቡብ ኮሪያ የኒውክሌር ውጭ የሆኑ አቅሞችን በመጠቀም የኒውክሌር መከላከልን ለመደገፍ በሚያስችሉ መንገዶችን ዙሪያ መወያየታቸውንም ተገልጿል።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ "ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ ወይም በአጋሮቿ እና ላይ የምትፈጽመው የትኛውም የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ተቀባይነት እንደሌለውና ምላሹ እስከ የአገዛዙን ፍጻሜ የሚያደርስ ሊሆን እንደሚችል የአሜሪካው ወገን አሳስቧል" ሲል ሚኒስቴሩ አስጠንቅቋል።