አሜሪካ በጀርመን ለዩክሬን ኃይሎችን የምትሰጠውን ስልጠና ልታስፋፋ ነው
በወር 500 የሚጠጉ ዩክሬናውያን ወታደሮች ስልጠናውን በጥር ወር ይጀምራሉ ተብሏል
የስልጠናው ትኩረት ወደፊት ሊወጡ ከሚችሉ መሳሪያዎች ይልቅ በመስክ ላይ ያሉ ስርዓቶች ላይ መሆኑን ፔንታጎን አስታውቋል
የአሜሪካ ጦር ሩሲያን የሚዋጉ የዩክሬን ወታደራዊ አባላትን በጋራ ለማንቀሳቀስ እና በተቀናጀ የጦር መሳሪያ ስራዎች ላይ በማተኮር በጀርመን የሚሰጠውን ስልጠና እንደሚያስፋፋ አስታወቀ።
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን) ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄኔራል ፓትሪክ ራይደር እንደተናገሩት በወር 500 ለሚጠጉ ዩክሬናውያን ስልጠናው በጥር ወር ይጀመራል።
ከሚያዚያ ወር ጀምሮ ከ15 ሽህ የሚበልጡ የዩክሬን ወታደሮችን አሜሪካና እና አጋሮቿ በማሰልጠን ኃይል እየገነቡ ነው ተብሏል።
አዲሱ የስልጠና ግፊት ባለፈው የካቲት ከሩሲያ ጋር ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ አሜሪካ እና የኔቶ አጋሮቿ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሚያወጡ ልዩ ወታደራዊ መሣሪያዎችን ከማቅረብ በተጨማሪ እንደሆነ ተነግሯል።
"የተጣመረ የጦር መሳሪያ ስልጠና ቀጣይነት ያለው የስልጠና ጥረታችን እርምጃ ነው" ሲሉ ራይደር በአንድ ጊዜ ጠላትን እንዴት ማጥቃት እንደሚቻል አመላክተዋል።
በጀርመን በግራፈንዎህር የሚገኘው 7ኛው የሰራዊት ማሰልጠኛ ኮማንድ በጀርመን ስልጠናውን እንደሚያካሂድ ፔንታጎን ተናግሯል።
ብርጋዴር ጄኔራል ራይደር የስልጠናው ትኩረት ወደፊት ሊወጡ ከሚችሉ መሳሪያዎች ይልቅ በመስክ ላይ ያሉ ስርዓቶችን መጠቀም ይሆናል ብለዋል።
ሮይተርስ እንደዘገበው አሜሪካ ለዩክሬን እጅግ በጣም ዘመናዊ ከሆኑት ስርዓቶች አንዱ የተባለውን የፓትሪዮት ሚሳይል መከላከያ ስርዓት ለማቅረብ እቅዷን እያጠናቀቀች ነው ብሏል።
ዩክሬን የኃይል መሠረተ ልማቷን ጨምሮ ከከባድ የሩሲያ ሚሳይል ቦምብ ለመከላከል በአሜሪካ የተሰሩ መከላከያዎችን ጨምሮ የምዕራባውያን አጋሮቿን የአየር መከላከያ ጠይቃለች።