ሩሲያ የሚሳኤል እጥረት እንደሌለባት ዩክሬን ገለጸች
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ሩሲያ አሁንም ለተከታታይ ግዙፍ ጥቃቶች በቂ ሚሳይሎች አሏት ብለዋል
ፕሬዝዳንቱ ምዕራባውያን አጋሮች ለኪየቭ ተጨማሪ እና ዘመናዊ የአየር መከላከያ ዘዴዎችን እንዲያቀርቡ አሳስበዋል
ሩሲያ የሚሳኤል እጥረት እንደሌለባት ዩክሬን ገለጸች
ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሩሲያ ባደረገችው ትልቅ የተባለ ጥቃት ከ70 በላይ ሚሳይሎችን በዩክሬን መተኮሷን የኪዬቭ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
ባለስልጣናቱ እንዳሉት ጥቃቱ በሀገሪቱ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ ኃይልን ያቋረጠ ሲሆን፤ ኪዬቭ የአደጋ ጊዜ እንድታውጅ አስገድዷታል።
በጥቃቱ በማዕከላዊ ክሪቪ ውስጥ አንድ አፓርታማ ተመቶ ሦስት ሰዎች ሲገደሉ እና በደቡብ ኬርሰን ደግሞ አንድ ሌላ ሰው መሞቱን ተናግረዋል።
በምስራቃዊ ዩክሬን በሩስያ የተመረጡ ባለስልጣናት ደግሞ በዩክሬን ጥቃት 12 ሰዎች መሞታቸውን ተናግረዋል።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በምሽት የቪዲዮ ንግግራቸው ላይ ሩሲያ አሁንም ለተከታታይ ግዙፍ ጥቃቶች በቂ ሚሳይሎች አሏት ብለዋል። እናም ምዕራባውያን አጋሮች ለኪየቭ ተጨማሪ እና የተሻሉ የአየር መከላከያ ዘዴዎችን እንዲያቀርቡ በድጋሚ አሳስበዋል።
ዘለንስኪ ዩክሬን ጥቃቱን ለመመከት ጠንካራ ናት ብለዋል።
"ከሞስኮ ሮኬት አምላኪዎች እንደሚፈልጉት ምንም ይሁን ምን በዚህ ጦርነት ውስጥ የኃይል ሚዛኑን አይለውጥም" ብለዋል።
የዩክሬን የጦር ኃይል አዛዥ ከ76 የሩስያ ሚሳኤሎች 60 ያህሉ በጥይት ተመተው ወድቀዋል።
ነገር ግን በጥቃቱ የኃይል ሚንስትር ቢያንስ ዘጠኝ የኃይል ማመንጫ ተቋማት መመታታቸውን ተናግረዋል።
ሮይተርስ እንደዘገበው ሞስኮ ጥቃቱ የዩክሬንን ጦር ለማሰናከል ያለመ እንደሆነ ተናግራለች።
የኪዬቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ ላይ እንደተናገሩት ከነዋሪዎች አንድ ሦስተኛው ብቻ ሙቀት እና ውሃ አላቸው፤ እንዲሁም 40 በመቶዎቹ ብቻ ኤሌክትሪክ አላቸው።
የሩስያ ጦር የዩክሬይንን አንድ አምስተኛው አካባቢ የተቆጣጠረ ሲሆን ብዙ ወታደሮች በአሰቃቂ ውጊያ መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ተዘግቧል። ምንም እንኳን አንዳቸውም ወገኖች ስለ ራሳቸው ወታደራዊ ጉዳት ዝርዝር መረጃ ባይሰጡም።