ሀገራቱ ስለ ሚሳይል ስጦታው እስካሁን በይፋ ማረጋገጫ አልሰጡም
አሜሪካ ለዩክሬን የረጅም ርቀት ሚሳይል እንደምትሰጥ ገለጸች፡፡
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ኪየቭን ለመርዳት ዘመናዊ የረጅም ርቀት ሚሳይል ለመስጠት አቅደዋል ተብሏል።
ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የአሜሪካ ባለስልጣናት ኪየቭ እስከ 300 ኪ.ሜ የሚምዘገዘጉ ሚሳይሎችን ልታገኝ መሆኗን ተናግረዋል።
መሳሪያው ዩክሬን በጦርነቱ ግንባር ሁነኛ የሩሲያ ኢላማዎችን ለመምታት ያግዛታል ተብሏል።
አርብ ዕለት ከዩክሬን ተገንጥላ ሞስኮን በተቀላቀለችው ክሪሚያ ኪየቭ የሩሲያ የጥቁር ባህር ዋና መቀመጫን በሚሳይል ደብድባለች።
በሴቫስቶቭል ወደብ የደረሰው ጥቃት ብሪታኒያና ፈረንሳይ ለኪየቭ ባቀረቡት መሳሪያ የተፈጸመ መሆኑን የዩክሬን የመከላከያ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ሩሲያ እና ዩክሬን በሱዳንም እየተዋጉ መሆኑ ተገለጸ
ጥቃቱ የምዕራባዊያን የመሳሪያ እርዳታ ተጽዕኖን ያሳየ ነው ተብሏል።
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን "አነስተኛ ቁጥር" ያላቸውን ሚሳይሎች እንደሚሰጡ ለዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ መናገራቸውን ምንጮች ተናግረዋል።
ዎል ስትሪት ጆርናል እንደዘገበው መሳሪያዎቹ በሚቀጥሉት ሳምንታት በኪየቭ እጅ ይገባሉ።
ሆኖም አሜሪካና ዩክሬን ስለ መሳሪያ ሪፖርቶች በይፋ አላረጋገጡም።