አሜሪካ በእስራኤል ጦር ላይ ማዕቀብ ለመጣል እያጤነች ነው ተባለ
አሜሪካ “ኔትዛህ ይሁዳ” በተባለ የእስራኤል ጦር ክፍለ ጦር ላይ ነው ማእቀብ የምትጥለው
የእስራኤ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ጦራቸው ላይ ማዕቀብ እንዳይጣል “ባለኝ አቅም ሁሉ እፋለማለሁ” ብለዋል
አሜሪካ “ኔትዛህ ይሁዳ” በተባለ የእስራኤል ጦር ክፍለ ጦር ላይ ማዕቀብ ለመጣል እያጤነች መሆኑ ተሰምቷል።
“ኔትዛህ ይሁዳ” ክፍለ ጦር በዌስት ባንክ አካባቢ በፍሊስጤማውያን ላይ ከፍተኛ የሆነ የመብት ጥሰት በመፈጸሙ ነው ማዕቀብ ይጠብቀዋል የተባለው።
“ኔትዛህ ይሁዳ” በተባለ የእስራኤል ጦር ክፍለ ጦር በዌስት ባንክ ውስጥ በሚገኙ ፍሊስጤውያን ላይ ያለ በቂ ማስረጃ መግደል እና የመብት ጥሰት እየፈጸመ እንደሆነ ወቀሳ ይርብበታል።
የእስራኤል ሌበር ፓርቲ መሪ ሜራቭ ሚካይሊ በትናንትናው አልት ያለ በቂ ማስረጃ ፍሊስጤማውያንን የሚገድለው “ኔትዛህ ይሁዳ” ክፍለ ጦር እንዲበተን ጥሪ ማቅረባቸው አይዘነጋም።
መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው አክሲዮስ የዜና ወኪል ቅዳሜ ዕለት እንደዘገበው ዋሽንግተን በዌስት ባንክ ውስጥ በሚንቀሳቀስ የእስራኤል “ኔትዛህ ይሁዳ” ሻለቃ ላይ ማዕቀብ ለመጣል አቅዳለች።
የእስራኤል መገናኛ ብዙሃንም ከሩብ ምዕተ ዓመት በፊት የተቋቋመ እና በጣም አክራ ኦርቶዶክስ አይሁዳውያን ወንዶችን በብዛት ያቀፈው “ኔትዛህ ይሁዳ” ሻለቃ የአሜሪካ ማዕቀብ ኢላማ መደረጉን ደርሰንበታል ብለዋል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በእስራኤል ወታደራዊ ክፍሎች ላይ ከመብት ጥሰት ጋር ተያይዘው የሚጣሉትን ማንኛውንም ማዕቀብ እንደማይቀበሉ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት እሁድ በሰጡት መግለጫ “በእስራኤል ጦር ክፍል ላይ ማዕቀብ ልጥል እችላለሁ ብሎ የሚያስብ ካለ በሙሉ ኃይሌ እታገላለሁ” ብለዋል።
የእስራኤል ጦር ካቢኔ ሚኒስትር ቤኒ ጋንዝ በበኩላቸው፤ በጉዳዩ ላይ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር መወያየታቸውን እና አሜሪከ ጉዳዩን በድጋሚ እንድታጤን ማሳሰባቸውን ተናግረዋል።
ጋንትዝ “እንደዚህ ዓይነት ማዕቀቦች በጦርነት ጊዜ የእስራኤልን ስለሚጎዱ ስህተት ነው” ብለዋል።