አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን የእርዳታ ቅነሳ ከግድቡ ጋር ማያያዝ ልታቆም ነው
ትራምፕ የሚመሩት የህዳሴ ግድብ ድርድር በመፍረሱ ምክንያት የኢትዮጵያን እርዳታ ቆርጠው ነበር
በአሜሪካ ጊዜያዊ እርዳታ ማቆም እርምጃ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ለልማትና ለጸጥታ የምትለግሳት 272 ሚሊዮን ዶላር ቀርቶባት ነበር
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ዋሽንግተን በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ በምታራምደው ፖሊሲ ምክንያት የተወሰኑ እርዳታዎች አቁማ ነበር፤ አሁን ማያያዟን ልታቆም መሆኑን አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ የህዳሴ ግድብ ድርድር በአሜሪካ ዋሽንግተን ተጀምሮ ነበር፡፡ ነገርግን በታዛቢነት የገባቸው አሜሪካ ሚናውን ወደ አደራዳሪነት እንዲሁም ወደ የስምምነት ሰነድ አርቃቂነት በማደጉ ምክንያት ኢትዮጵያ አልቀበለም በማለቷ የአሜሪካው ድርድር ተቋርጧል፡፡
የውጭ ገዳይ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ እንዳሉት የፕሬዘዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር አሜሪካ በህዳሴው ግድብ ላይ የምትከተለውን ፖሊስ እንደምትከልስና አስተዳደሩ በሶስቱ ሀገራት በካከል ያለው ድርድር መፍትሄ እንዲያገኝ ሊኖረው የሚችለውን ሚና ያጠናል ብሏል፡፡
የታላቁ የኢትጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌት ባለፈው ሀምሌ ወር ነበር የተሞላው፡፡ ኢትዮጵያ ግድቡን እንደምትሞላ በምትገልጽበት ጊዜ ሱዳንና ግብጽ የኢትዮጵያን የብቻ እርምጃ እንደማይቀበሉት በተደጋጋሚ ገልጸው ነበር፡፡
ቃል አቀባይ ፕራይስ ኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያደርጉትን ገንቢ ጥረት አሜሪካ እንደምትደግፍ ገልጸዋል፡፡
የአሜሪካ ጊዜያዊ እርዳታ ማቆም እርምጃ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ለልማትና የጸጥታ የምትለግሳት 272 ሚሊዮን ዶላር እንቀረባት የገለጹት ፕራይስ በበርካታ ምክንያቶች የቆመው እርዳታ የሚመለሳበትና እንደሚታይና ውሳኔውንም ኢትዮጵያ እንድታውቅ ይደረጋል ብለዋል፡፡
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሚመሩት የህዳሴ ግድብ ድርድር በመፍረሱ ምክንያት የኢትዮጵያን እርዳታ ቆርጠው ነበር፡፡ በፈረንጆቹ መስከረም አሜሪካ የ100 ሚሊዮን እርዳታ ከልክላ ነበር፡፡
ኢትዮጵያም ትራምፕ በኢትዮጵያ ግብጽ ግጭት ሊያስነሳ የሚችል ንግግር አድርገዋል በሚል በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር ጠርታ ማነጋገሯ ይታወሳል፡፡