አሜሪካ ዜጎቿ ሞስኮን ለቀው እንዲወጡ ያስተነቀቀችው ሩሲያ ለተጠባባቂ ጦሯ ጥሪ ማቅረቧን ተከትሎ ነው
አሜሪካ ዜጎቿ ሩሲያን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ አዘዘች።
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባሳለፍነው ሳምንት 300 ሺህ ለሚሆኑ የሩሲያ ተጠባባቂ ጦር አባላት ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ይሄንን ተከትሎም አሜሪካ በሩሲያ የሚኖሩ ዜጎቿ ሞስኮን ለቀው እንዲወጣ አስጠንቅቃለች።
አሜሪካ በተለይም የሩሲያ እና አሜሪካ ጥምር ዜግነት ያላቸው ዜጎች ሞስኮን ለቀው እንዲወጡ ማዘዟን ቪኦኤ ዘግቧል።
ሩሲያ በተለይም ጥምር ዜግነት ያላቸው ዜጎች ወደ አሜሪካ ኢምባሲ እንዳይሄዱ እና ከሩሲያ እንዳይወጡ ልትከለክል እንደምትችል ተገልጿል።
አሜሪካዊያንም ወደ ሩሲያ እንዳይጓዙ ያስጠነቀቀች ሲሆን በሩሲያ የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ዜጎች በተዘጋጀላቸው የንግድ አውሮፕላኖች ታግዘው እንዲወጡ ስትልም ዋሸንግተን አስታውቃለች።
እንዲሁም በተሽከርካሪ በመጓዝ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ሞስኮን ለቃችሁ ውጡ ያለችው አሜሪካ ይህ እድል ሊቆይ አይችልም ተብሏል።
በሞስኮ ያለው የአሜሪካ ኢምባሲ በሩሲያ ላሉ አሜሪካዊያን ድጋፍ ለማድረግ ብዙ ውስንንቶች ስላሉበት ዜጎች በራሳቸው ወጪ እንዲጓዙ ተናግሯል።
በሩሲያ ያሉ አሜሪካዊያን ራሳቸውን ከየትኛውም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁም አሜሪካ አሳስባለች።
የትኛውንም የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን ጨምሮ በግላቸው የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይም ማንኛውንም ነገር ከማጋራት እንዲቆጠቡ አሜሪካ አሳስባለች።
ሩሲያ በአሜሪካ ስለተሰጠው ማሳሰቢያዎች እስካሁን በይፋ የተናገረችው ነገር የለም።