አሜሪካ ቻይና አዲስ የዓለም መዋቅር ለመመስረት እየሰራች መሆኑን ገለጸች
ሩሲያን ከተቀረው ዓለም ለመነጠል እየተደረገ ባለው የምዕራባዊያን ጥረት ውስጥ ዋነኛ የሞስኮ ሚዛን አስጠባቂ ሆናለች
ቻይና ለአሜሪካ ቁጥር አንድ ጠላት መሆኗን የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር አዛዥ ሎይድ ኦስቲን ገልጸዋል
አሜሪካ ቻይና አዲስ የዓለም መዋቅር ለመመስረት እየሰራች መሆኑን ገለጸች።
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ስምንት ወራት የሞላው ሲሆን በየጊዜው አዳዲስ ክስተቶችን ማስተናገዱን ቀጥሏል።
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን እንዳሉት ቻይና አዲስ የዓለም መዋቅር ለመፍጠር እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል።
እንደ ፔንታጎን አዛዥ ገለጻ ከሆነ አሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባውያን ሀገራት አሁን ያለውን የዓለማችንን መዋቅር እየመሩ ሲሆን ቻይና ከዚህ ተቃራኒ የሆነ መንገድ ለመፍጠር እየሰራች መሆኑን ኮንነዋል።
ይሄንን ተከትሎም ቻይና የአሜሪካ ቁጥር አንድ ጠላት ሀገር ነች ያሉት ዋና አዛዡ ቻይና አዲስ የዓለም ስርዓትን ከመፍጠር አንጻር ብቸኛዋ ተፎካካሪ ሀገር መሆኗንም ተናግረዋል።
ዋና አዛዡ አክለውም በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ምክንያት ሞስኮን ከተቀረው ዓለም ለመነጠል እየተደረገ ባለው ጥረት ቻይና ከጀርባ ሆና እያገዘቻት እንደሆነም ጠቁሙዋል።
ሩሲያ የወቅቱ የአሜሪካ ስጋት ነች ያሉት ዋና አዛዡ ቻይና ግን በተለይም የኢንዶ ፓስፊክ አካባቢን እና ዓለም አቀፍ ግንኙነትን በአዲስ መንገድ አዲስ ግንኙነት መመስረት እንደምትፈልግም ተናግረዋል።
ሩሲያ በአሜሪካ ወዳጅ ሀገራት ላይ የኑክሌር፣ ሳይበር እና ኬሚካል ጥቃቶችን የመፍጠር ስጋት መደቀኗንም ዋና አዛዡ ገልጸዋል።
እነዚህ የአሁን እና የረጅም ጊዜ የአሜሪካ ጠላት የተባሉት ቻይና እና ሩሲያ አዳዲስ ትብብሮችን በመፍጠር ላይ መሆናቸውን ዋና አዛዡ ጠቅሰዋል ሲል የጀርመን ድምፅ ዘግቧል።
ዋና አዛዡ አክለውም ኢራን እና ሰሜን ኮሪያም የኑክሌር ጦር መሳሪያ ለመታጠቅ ሙከራቸውን አስፋፍተዋል ያሉት ዋና አዛዡ እነዚህ ሀገራት አሜሪካ በምትፈልጋቸው አካባቢዎች ያሉ ጸረ ዋሸንግተን ሀገራት ናቸውም ብለዋል።
አሜሪካ ከሩሲያ ጋር በቀጥታ ጦርነት ውስጥ ላለችው ዩክሬን የጦር መሳሪያ በመርዳት ላይ ስትሆን ባለፉት ስምንት ወራት ውስጥ 18 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን ረድታለች።