ፑቲን “ምዕራባውያን በዓለም ጉዳዮች ላይ ያላቸው የበላይነት እያከተመ ነው” አሉ
ከ2ኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ዓለም እጅግ አደገኛ የሆኑ አስርት ዓመታት ተጋርጦባታል ብለዋል
ፑቲን ምዕራባውያን በዓለም ላይ ትርምስ በመዝራት አደገኛ፣ ደም አፋሳሽና ቆሻሻ' ጨዋታ እየተጫወቱ ነው ብለዋል
የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ወዲህ አለም እጅግ አደገኛ አስርት ዓመታት ተጋርጦባት እንደቆየ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳት ፑቲን በትናንትናው እለት በቫልዳይ የውይይት ክለብ አለም አቀፍ የፖሊሲ ባለሙያዎች ኮንፈረንስ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ አሜሪካ በዩክሬን ያለው ግጭት አአነሳስታለች ሲሉ ከሰዋል።
“ምዕራባውያን እየተከተሉት ያለው እንደ አደገኛ፣ ደም አፋሳሽ እና ቆሻሻ ጂኦፖለቲካዊ ጨዋታ በዓለም ዙሪያ ትርምስ እየፈጠረ ነው” ሲሉም ፕሬዝዳቱ ተናረዋል።
ፕሬዝዳት ፑቲን በንግግራቸው አክለውም፤ ምዕራባውያን ስለ ዓለም የወደፊት እጣ ፈንታ ከሩሲያ እና ከሌሎች ኃያላን ሀገራት ጋር መነጋገር አለባቸው ሲሉም ተግናረዋል።
ምዕራባውያን በዓለም ጉዳይ ላይ ያላቸው ታሪካዊ ያልተከፋፈለ የበላይትጊዜ እያበቃ መሆኑንም ፑቲን በንግግራቸው አንስተዋል።
“አሁን ታካዊ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን፤ ከፊትለፊታችን ያለው በጣም አደገኛ እና የማይገመት ሊሆን ይችላል” ያሉት ፑቲን፤ በተቃራኒው ግን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ወሳኙ አስርት ዓመታት ሊሆን ይችላል ሲሉም ተናግረዋል።
አሁን ካለው ያለመግባባት በዘለለ ሩሲያ ምእራባውያንን የሩሲያ ጠላት አድርገን አንወስድም ሲሉም ተናግረዋል።
ፑቲን በንግግራቸው አክለውም “ሞስኮ ለምዕራቡ ዓለም መሪ ሀገሮች እና ኔቶ አንድ መልዕክት አላት፤ ይህም ጠላት መሆናችንን እናቁም፤ አብረን እንኑር” የሚል ነው ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል።