ቻይና በህገ ወጥ መንገድ ወደ ባህር ክልሏ የገባ የአሜሪካ የጦር መርከብ አባረርኩ አለች
በቀጣናው በአሜሪካ እና በቻይና መካከል ያለው ውጥረት እየጨመረ መጥቷል
ቻይና የአሜሪካ የጦር መርከብ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ ቻይና የባህር ክልል መግባቱን አስታውቃለች
ቻይና የአሜሪካ የጦር መርከብ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ ቻይና የባህር ክልል መግባቱን አስታውቃለች
የቻይና ጦር በደቡብ ቻይና ባህር ውስጥ በፓራሴል ደሴቶች ዙሪያ በህገ-ወጥ መንገድ ገባ ያለውን የአሜሪካን የጦር መርከብ እንዳባረረም ገልጿል።
የጦር ኃይሉ በመግለጫው ከመንግስት እውቅና ውጪ የፀረ ሚሳዔል መርከብ በቻይና ግዛት ውስጥ በህገ-ወጥ መንገድ ገብቷል ነው ያለው።
- ቻይና ፤ አሜሪካ በታይዋን ጉዳይ ቀይ መስመር እንዳታልፍ ስትል አስጠነቀቀች
- ሩሲያ “የውሃ ክልሌን የጣሰ የአሜሪካ የባህር ሰርጓጅ መርከብ አሳድጄ አባረርኩ” አለች
የመርከቡ መግባት በተጨናነቀው የውሃ መስመር ላይ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር አድርጓል ብሏል።
የቻይና ደቡባዊ ዕዝ ቃል አቀባይ ቲያን ጁንሊ "የዕዙ ኃይሎች በማንኛውም ጊዜ በከፍተኛ ንቃት ሁኔታን በመጠበቅ ብሄራዊ ሉዓላዊነትን እና ደህንነትን ይጠብቃሉ” ብለዋል።
እንዲሁም “በደቡብ ቻይና ባህር ሰላምና መረጋጋትን በቆራጥነት ለማስጠበቅ አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃ ይወስዳሉ" ሲሉም አስታውቀዋል።
በቀጣናው በአሜሪካ እና በቻይና መካከል ያለው ውጥረት እየጨመረ መጥቷል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ቤጂንግ የግዛት ይገባኛል ጥያቄዋን ለማራመድ ስትፈልግ አሜሪካ በደቡብ ቻይና ባህርና በታይዋን የባህር ዳርቻ ላይ ቻይና ያላትን አቋም ለመቃወም በእስያ-ፓሲፊክ ትብብሮችን ስትፈጥር ቆይታለች።